የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል፡፡እስካሁን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፡–በዘንድሮው…

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

እስካሁን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፡-

-በዘንድሮው ምርት ዘመን ከፍተኛ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር አለ፤ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ምርታማነት ችግር እንደሚፈጥር እየታወቀ ለምን ትኩረት አልተሰጠውም? በቀጣይስ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ይፈታል ወይ? በሀገር ውስጥ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ምን ታስቧል?

-የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን ላይ የደረሰበት አፈጸጸም ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

እንደ ገበታ ለሀገር ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ ሀገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ትችቶች ይነሳሉ፤ ከዚህ አንጻር የፕሮጀክቶቹ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላይ ማብራሪያ
ቢሰጥ?

-ኤርትራን ጨምሮ አሁን ላይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዎያን

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply