
መንግሥት እና ታጣቂውን ቡድን ለማሸማገል የአፍሪካ ኅብረት ጣልቃ እንዲገባ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ እንደራሴዎች ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናገሩ። አስራ ሁለት በኦሮሚያ ክልል የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት የሕዝቡን ሕይወት እና ንብረት እያወደመ በመሆኑ፣ ትኩረት እንዲያገኝ በሚያደርጉት ጥረት ለአፍሪካ ኅብረት ጥሪ ማቅረባቸውን እንደራሴዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Source: Link to the Post