የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተባለ፡፡የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በጥቅምት ወር በነበረው እንደሚቀጥል…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/J0pmwhZjPo1LYIWT3xh5ZE-gp7XTs9a7aKDrs2OC6tQoE63gcoTkbc-3fPoHPdefQCPtcW4h0j3rORohs76Era7C_c6y8eFs4GcdxDaKG3wYIKWOtFdwtg34ex0_MpOOjpuOuVZQEYiSAsHJ6vVdRY3f8uzOHJBqsYScdpm49uAvuAg9ic8tLJw_MEAZmWB2aUrrYiQUM7lRtSRhQisikk-DzWcx6gqTnpC2XmYupDLwGNH9mnRTO2vTO8e3N1vjYYE8ToKZ2YLqvCGwy3zOt_Y3V-Lxg8TMtZtYcRJxMQ-9Tt9JqZIZE5MilImPMINz_GNRT2UMcb-Q3mcG94BzAQ.jpg

የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተባለ፡፡

የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በጥቅምት ወር በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ጀምሮ ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

በዚህም በሕዳር ወር 2015ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅን በተመለከተም በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው መሰረት አዲስ አበባ ላይ በሊትር 74 ብር ከ99 ሣንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን
ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply