You are currently viewing የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? አሻራ ሚዲያ  ሰሜን አሜሪካ  የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? “የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለ…

የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? “የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለ…

የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ የሕግ ማስከበር ትርጉሙ ከመቼ ጀምሮ ነው የተቀየረው? “የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው” ብለዋል ዶ/ር ይልቃል ከፋለ። ጎንደር ላይ ሰኔ 5/2014 እየተደረገ ባለው ስብሰባ_ እስኪ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የማክሰኝቱን አስነዋሪ የእርኩስ መናፍስት ደም የማፍሰስ ተግባርን ለምን ብለን እንጠይቅ? እስኪ በጣቁሳ ወረዳ ደልጊ በጀግኖቻችን ላይ እየሆነ ያለውን እንጠይቅና መልስ የሌላቸው መሆኑን እናረጋግጥ? እስኪ ጎንደር ላይ የታፈኑትን ስለአማራ ብሎም ስለኢትዮጵያ አንድ አይሉ ሁለቴ የሞቱት የእነ ሻለቃ አንተነህ ድረስን “ወደ ወልቃይት መሳሪያ ይዛችሁ ማለፍ አትችሉም” በሚል የተከለከሉትንና ወደ እስር የተጋዙትን ጉዳይ አንስተን እንሞግት? በሕግ ጉዳዩ እየታዬ ከሰነበተ በኋላ የ20 ሽህ ብር ዋስትና እንዲከፍል ተደርጎ ከአንገረብ ማ/ቤት በር ላይ አሳፍነው ወደ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ስለላኩት የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ እንጠይቅ እና የጨዋታ ህጉ የተቀየረ መሆኑን እናረጋግጥ? የትኛው ይሆን ሕግ ማስከበሩ? አፈናውን ነው? የአማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ ከሞት የታደገን ፋኖ ሰለሞን አጠናው ጫካ የገባው ለመዝናናት መሰለን ወይ? እስኪ እንጠይቅ እነ አርበኛ መብራቱ አረጋ ከጠላት የማረኩትን ብሬን ቀምተው ሊያፍኗቸው ሲሆን ምርጫቸውን ጫካ ያደረጉት ከተማ ጠልተው ይሆን? አዲስ ዘመን ላይ የገደላችኋት የጀግናዋ ፋኖ ካሳዬ አልቃድር ደም በእውነት በምድርም በሰማይም ይፋረዳችኋል! በሉ እስኪ ንገሩን ትናንት ድረሱልን ብላችሁ ኡኡ ስትሉ የደረሱላችሁን፣ ከመታነቅ ያዳኗችሁን፣ከሀገር ለመኮብለል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ስትከፋፈሉ የነበራችሁ አካላት ተመልሳችሁ በህዝብ ላይ ጦርነት ማወጃችሁ ነው ህግ ማስከበር? ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ በመርዓዊ፣ በእናሸንፋለን ቀበሌ እና አካባቢው ያፈሰሳችሁት የንጹሃን ደም ይፋረዳችኋል! እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን፣ እነ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን፣ እነ አስረስ ማረ ዳምጤንና ሌሎችንም በጠላትነት ፈርጃችሁ በሽህ የሚቆጠር ጦር በየቀበሌው በማዝመት አርሶ አደሩ እንዳያለማ ማስጨነቅ፣ማፈንና ማሳደድ ይሆን ህግ ማስከበር? በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ባለው በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ልብስ “ምግብ ስጡን” ብሎ በአማርኛ መናገር የማይችል አካላን አልብሶ በማስገባት በህዝብ ላይ ማዘመት ነው ህግ ማስከበር? ትርጉሙ ተቀዬረ እንዴ? የተለዬ አስተሳሰብ ያለውን በጠላትነት ፈርጆ የሚያጠቃው ስሙን ከመቀያየር ውጭ በግብር ከትናንት ያልተፋታውን ብአዴንን ያልደገፉትን በማጥፋት ነው ልሙጥ ብአዴናዊያንን ለመፍጠር ታስቦ ሲሰራ ነው የህዝብ አንድነት የሚመጣው? በየትኛው የህግ ቋንቋ? በአፋኞች ዘንድ ትክክል ሊሆን ይችላል። ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ መሃል ከተማ ላይ ያፈሰሳችሁት የንጹሃን ደምም ሁሌም ይፋረዳችኋል! በየጁቤ ኮርክ የፈጸማችሁት ጥቃት ነው ሕግ ማስከበር? ስንት የፋኖ አባላትን በቡድን መሳሪያ ገደላችሁ? በወልድያ ንጹሃን ላይ የፈጸማችሁት ጭፍጨፋ ነው ህግ ማስከበር? ደቡብ ወሎ ሀርቡ ላይ ለ4 ቀናት በከፈታችሁት ጦርነት ስንቱን የህዝብ ልጅ ገደላችሁ? ከሀርቡ እስር ቤት ቀጥቅጣችሁ የገደላችሁት የፋኖ ሲራጅ መሀመድ ደም ወደ ፈጣሪ ይጮሃል! በሰሜን ወሎ ሀብሩ መርሳ እና አካባቢው ማርኮ እና በገንዘቡ ገዝቶ የታጠቀውን ትጥቅ በኃይል ማስፈታት ነው ወልቃይት ቀይ መስመራችን ናት ማለት? “የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ሲሉ ጌታዎም ሆነ እርስዎ ህዝቡን ሳያሳትፉ ተደራደሩ አልተደራደሩ ምን ትርጉም ያመጣል? የወልቃይት ጉዳይ በጅምላ እየተጨፈጨፈ ያለው የአማራ ህዝብ ብሎም የፍትህና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው። ከ1,642 በላይ አማራዎች ተለይተው በአንድ ቀን የተጨፈጨፈባትንና በደም ጎርፍ የጨቀዬችውን ማይካድራን፣ ቦዛንና ጭናን፣ አዳርቃይን፣ቆቦን እንዲያው በጥቅሉ በጅምላ ዘሩ በየቀኑ እየጠፋበት ያለውን መላ አማራን ያላሳተፈ የጓዳ ውስጥ ድርድር ምን ይፈይዳል? የትናንት ክህደታችሁን አጠናክሮ የማስቀጠል የእርኩሳን ከሃዲዎች መንገድ ምን ትርፍ ያስገኛል? ለመሆኑ “የወልቃይት ጉዳይ ቀይ መስመር ነው” ስትሉ የሌላውን ጉዳይስ ምን ልትሉት ይሆን? ወልቃይት ስትሉ ጠገዴንና ጠለምትን አካታችሁ ይሆን? እንዲያው ለመሆኑ የጠገዴ፣የጠለምት፣የራያን፣የመተከልን፣ የደራንና የዋግኸምራ ሁለት ወረዳዎችን ጉዳይስ ምናችን ናቸው ትሏቸው ይሆን? ዛሬም እንደ ትናንቱ አሳልፋችሁ ልትሰጡ አሰባችሁ? ለመሆኑ ይሳካላችሁ ይሆን? ለመሆኑ ሕዝቡ የሚያዋጣውን መንገድ የማያውቅና የማይገነዘብ ይመስላችኋል? እስከ መቼ በዚህ መንገድ ለመቀጠል ትችላላችሁ? ሁሉም ነገር ወደ ፊት የሚታይ ይሆናል! ጊዜ ዳኛ ነው። ታሪክ ይፋረዳችኋል! በዚህ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ደግሞ የሚከተለውን ምላሽ አጋርተዋል:_ በብዙ ነገር ከናንተ ጋር እንለያያለን። በብዙ ነገርም እንራራቃለን። በዚህ ጉዳይ ግን አንድ ነን። በኛም በኩል የአማራ ታሪካዊና ነባራዊ ርስቶች ጉዳይ ለድርድር የማናቀርባቸው ቀይ መስመሮቻችን ናቸው። — ወልቃይት ― መተከል ― ራያ ― ደራና ሌሎችም የሸዋ አማራ አጽመ ርስቶች ለድርድር የማይቀርቡ የአማራ ቀይ መስመሮች ናቸው የአማራ ቀይ መስመሮች ላይ የተደራደረ የአማራ መሪም ሆነ በአማራ ቀይ መስመር ላይ ለመደራደር የሞከረ ማንኛውም የኢትዮጵያ መሪ ከታሪክ ይሰረዛል። ዘገባው የአሚማ ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply