የመለስ አካዳሚ በኢትዮጵያ ግዙፍ የህጻናትና እናቶች ሆስፒታል ሆነ

የመለስ አካዳሚ በኢትዮጵያ  ግዙፍ የህጻናትና እናቶች  ሆስፒታል ሆነ

ከዓመታት በፊት የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ እንደሚሆን ታስቦ የተጀመረው ህንፃ 700 ሚሊዮን ብር ወጪ ተመድቦለትና ግንባታው  ለሆስፒታል እንዲሆን ተሻሽሎ ተሰርቶ፣  በአገራችን ግዙፍና ዘመናዊ የህጻናትና እናቶች ሆስፒታል እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በ22 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና አያት ሜቆዶኒያ አካባቢ የሚገኘው ይኸው ሆስፒታል፤ ከትናንት በስቲያ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ማዘር ቴሬዛ እየተባሉ በሚጠሩት በጎ አድራጊ ወ/ሮ አበበች ጎበና ስም እንዲሰየም የተደረገው ዘመናዊ ሆስፒታሉ፤ ዘመኑ የደረሰባቸውን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ያሟላና በብቁ ባለሙያዎች የተደራጀ ነው ተብሏል፡፡ ሆስፒታሉ ለተገልጋዮች ወረቀት አልባ መስተንግዶ ለመስጠት የሚያስችል ሲሆን ከ400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
ሆስፒታሉ 100 የሚሆኑ የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ለሰባት እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎቶች ለመስጠት የሚያስችል ክፍሎች አሉት፡፡ በሆስፒታሉ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ሆስፒታሉ በስማቸው የተሰየመላቸው በጎ አድራጊዋ የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply