የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)  በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አመራር፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉና በአዲስ አበባ የሚገኙ አመራሮችና…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አመራር፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉና በአዲስ አበባ የሚገኙ አመራሮችና…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አመራር፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉና በአዲስ አበባ የሚገኙ አመራሮችና አባላቱም የደም ልገሳ መርሀ ግብሩን ዛሬ ማስጀመራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ከሆነው ከወጣት ለገሰ ወልደ ሀና ጋር ካደረገው ቆይታ እንደተረዳው መኢአድ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ሲል እንደ ድርጅት መመሪያ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት የመከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ እና ሚሊሻዎች በሕወሓት ላይ እየወሰዱት ባለው እርምጃ ጉዳት ለሚደርስባቸውና የወገንን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በሚል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የደም ልገሳ መርሀ ግብር አዘጋጅቷል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ የመኢአድ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች በአቅራቢያቸው ባለ የቀይ መስቀል ማህበር ተቋም በማቅናት ደም እንዲለግሱ አቅጣጫ ከመስጠት ባሻገር በማዕከል ደረጃ ዛሬ የደም ልገሳውን አስጀምሯል። በመኢአድ የምስራቅ ቀጠና ኃላፊ በአቶ ታጠቅ አሰፋ የተመራው የመኢአድ አመራሮችና አባላት ስብስብ ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ስተዲዬም አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጽ/ቤት በማቅናት የደም ልገሳ ማድረጋቸውን ወጣት ለገሰ ወልደ ሀና አስታውቋል። መኢአድ ሕወሓት በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ላይ የፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፍና መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ የድርሻውን እንዲያበረክት ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply