የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃወመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃወመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃወመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በአገራችን ባለው ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ፓርቲዎች በጋራ ለመምከርና ለመወያየት ብሎም ሀገራዊ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ምክር ቤት ነው ሲል ጠቅሷል። ይሁን እንጅ ምክር ቤቱ ከተቋቋመለት አላማና ግብ በማፈንገጥ ሁሉንም ባለድርሻ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳያወያይና ሳያማክር በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መግለጫዎችን ሲሰጥ እንደሚስተዋል ጠቁሟል። እንዲህ አይነት ደካማ አሰራር የተወሰኑ ቡድኖችንና ግለሰቦችን አላማ ለማስፈፀም ተብሎ የሚደረግ እንቅስቃሴ በመሆኑ ፓርቲያችን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) በአስቸኳይ ሊታረም ይገባዋል ብሎ ያምናል ሲል መኢአድ አስታውቋል። መኢአድ የጋራ ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ማለትም በ27/02/2013 ዓ.ም የፌደራል መንግስቱ ከህወሓት ጋር የፈጠረውን ጦርነት በድርድር መፍታት አለበት የሚል ፤ በማር የተለወሰ መርዝ ይዘት ያለው መግለጫ አውጥቷልም ብሏል። ሕወኃት ሕገ-መንግስቱን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን እና አጠቃላይ የአገሪቱን ሕግጋት በመጣስ ከመንቀሳቀሱም በላይ በዜጎችና በአገራችን ኅልውና ላይ አደጋ የደቀነ በመሆኑና በተለይ በአሁኑ ሰአት በአገራችን የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፍቶ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰና በአማራ ሕዝብ ላይም ወረራና ጥቃት እየፈፀመ ያለ ድርጅት በመሆኑ የጋራ ምክር ቤቱ የፌደራል መንግስት በወሰነው መሰረት ትብብር እና ድጋፍ የማድረግ ሚናውን ብቻ እንዲወጣ ስንል እናሳስባለን ነው ያለው መኢአድ በመግለጫው። የህወሓት ቡድን በሀገሪቱ እና በመከላከያ ሠራዊት ላይ ለፈፀመው ወንጀልና ክህደት በህግና በህግ አግባብ ብቻ ሊዳኝ ይገባልም ብለን እናምናለን ሲል አቋሙን ግልፅ አድርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply