You are currently viewing የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በድርጅቱ አመራር በመምህር ዘመነ ጌቴ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የሕግ ጥሰትን ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ለ7 የተለያዩ ተቋማትና…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በድርጅቱ አመራር በመምህር ዘመነ ጌቴ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የሕግ ጥሰትን ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ለ7 የተለያዩ ተቋማትና…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በድርጅቱ አመራር በመምህር ዘመነ ጌቴ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የሕግ ጥሰትን ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ለ7 የተለያዩ ተቋማትና አካላት በማሳወቅ በአስቸኳይ እንዲቆም ብሎም ከላይ እስከ ታች ያለው የፍ/ቤት ትዕዛዝ ተከብሮ ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ደብዳቤውን የጻፈው ለሚከተሉት 7 የተለያዩ ተቋማትና አካላት ነው። 1) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ 2) ለኢፌድሪ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ 3) ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ /ኢሰመጉ፣ 4) ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን/ ኢሰመኮ፣ 5) ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ለወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ 6) ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፣ 7) ለኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከድርጅቱ አመራር መምህር ዘመነ ጌቴ እስር አኳያ የሰብዓዊ መብት እና የሕግ ጥሰትን እያጋጠመ መሆኑን በመግለጽ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በሚል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በደብዳቤ መጠየቁን ቦርዱም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በደብዳቤ ጠይቆ በፖሊስ ኮሚሽን በኩል የተሰጠውን መልስ ማጋራቱን በማስታዎስ ላደረገው ከፍተኛ ጥረት ምስጋና በማቅረብ በድጋሚ ደብዳቤ ለመፃፍ መገደዱን በማስታወቅ ክትትሉ እንደሚትቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን ገልጧል፡፡ መኢአድ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር የሆነው መምህር ዘመነ ጌቴ ቦጋለ ከህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ፖለስ ኮሚሽን አሁን ደግሞ ሜክስኮ በሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተዛውሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ በደብዳቤው አመላክቷል፡፡ በተጠረጠረበት የሁከትና ብጥብጥ ወንጀልም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመቅረብም ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የቀረበበት ክስ ዋስትና የማያስከለክለው በመሆኑ ጉዳዩን ከእስር ውጪ ሆኖ እንዲከታተል በ5,000 (በአምስት ሺህ ብር ዋስትና ወስኗል ብሏል፡፡ ይሁን እንጅ የፍ/ቤቱ የመፍቻ ትዕዛዝ ቢቀርብለትም ይግባኝ ብያለሁ በማለት ፖሊስ ትዕዛዙን ሊቀበል አለመቻሉ ተገልጧል። ይህ ብቻ ሳይሆን ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበው ቢሆንም የእስር ፍ/ቤቱ የሰጠው የዋስትና መብት የሚያስከለክለው ባለመሆኑ፤ በተፈቀደው ዋስትና መሠረት ከእስር እንዲፈታ ሲል ውሳኔ ማሳለፉን መኢአድ ጠቅሷል፡፡ የከፍተኛውን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በድጋሚ አልቀበልም በማለት፤ እንደገና ለጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በማለት መ/ር ዘመነ ጌቴን ስለማቅረባቸውም አመላክቷል፡፡ የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም “በቀረበው የይግባኝ ጉዳይ ላይ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተሰርቷል” ለማለት አልቻለም፡፡ በመሆኑም መዝገቡ በሰበር ችሎት አይቀርብም በማለት የእስር ፍ/ቤቶቹ በሰጡት ውሳኔ መሠረት የፖሊስን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ ተከሳሹ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የውሳኔው ግልባጭ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግን አሁንም ለ3ኛ ጊዜ የፍ/ቤት ትዕዛዝን ባለመቀበል እና እስረኛውን ከመፍታት ይልቅ ከፍ/ቤት እንደተመለሰ እኛ ዘንድ የለም የሚል መልስ በመስጠት የአመራራችንን ሰብዓዊ እና ሕጋዊ መብቱን በመንጠቅ ከፍተኛ የሆነ የሕግ ጥሰት እየፈፀመብን የሚገኝ መሆኑን እንገልጻለን ብሏል፡፡ መኢአድ እንደዚህ አይነቱ ድርጊት በድርጅቱ አመራሮችና አባላት ላይ ላለፉት 27 ዓመታት ሲፈፀምባቸው እንደነበር እና አሁንም እየተፈፀመባቸው መሆኑን ቦርዱ፣ጠ/ሚኒስትሩ፣ የጠ/ፍ ፕሬዝዳንቷ፣ኢሰመጉ፣ኢሰመኮ እና እንባ ጠባቂ ተቋም በውል እንዲገነዘቡ እና በፖሊስ እምብኝተኝነት እየተዛባ ያለውን የፍትህ አካሄድ በማስተካከል የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ጠይቋል። መኢአድ እና አባላቱ በፕሮግራምና በፖሊሲ ከመታገል ውጪ መቼም ቢሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ወይም በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝም ሆነ አገራችንን እና ሕዝባችንን ለመጉዳት የተንቀሳቀሰበት ጊዜ አለመኖሩን በማስታዎስ ዳሩ ግን መንግስት በአመራሮቻችን ላይ ያልተገባ ስም በመስጠት እንግልት እያደረሰብን ነው ሲል አካሄዱን አውግዟል። ይባስ ብሎ የጠቅላይ ፍ/ቤቱን ውሳኔ ካለመቀበሉም በላይ አሁን ላይ መ/ር ዘኘነ ጌቴን በፌደራል ፖሊስ እሥር ቤት አስሮት የሚገኝ ሲሆን፣ ሌላ የሽብር ክስ በሚል አዳዲስ ምክንያት በመፍጠር ላለመፍታት ፖሊስ የሚሄድበት ሕገ-ወጥ መንገድ የሕጉን አፈፃፀም ምንነት በግልጽ እንደሚያሳይ ድርጅቱ ጠቁሟል። ስለዚህ የሥርዓቱን ትክክል ያለመሆን ፊት ለፊት ተቃውመናል፣ ተችተናል፣ ወደፊትም ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ ይህ ትግላችን የተቋቋምንበት መርሀችን ስለሆነ የሚቀጥል ይሆናል ብሏል መኢአድ በመግለጫው፡፡ በድርጅቱ አባላት ላይ ምክንያት እየተፈለገ የሚደርሰውን ማዋከብ፣ እስር፣ ሰብአዊና የሕግ ጥሰትን ቦርዱ እንዲያጣራው ብሎም ለፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች መቆሙን እንዲያሳውቅልን እና በድጋሚም ውሳኔ እንዲሰጥበት ሲል መኢአድ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ የፍርድ ቤቶቹንም ውሳኔዎችንም አባሪ አድርጎ ማቅረቡን በመግለጽ ለሚደረግለት ሕጋዊ ትብብር ከወዲሁ ምስጋናውን ስለማቅረቡ በፓርቲው ፕሬዝደንት በአቶ ማሙሸት አማረ ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ አመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply