የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በማይካድራው የጅምላ ፍጅት፣በመተከልና በሰገን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ወገኖችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያሰ…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በማይካድራው የጅምላ ፍጅት፣በመተከልና በሰገን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ወገኖችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያሰ…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በማይካድራው የጅምላ ፍጅት፣በመተከልና በሰገን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ወገኖችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያሰበ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከሀዲው ሕወሓት ባሰማራው ነፍሰ ገዳይ ቡድን በማይካድራ አማራዎች ላይ የተፈፀመው የጅምላ ፍጅት እንዲሁም በመተከልና በሰገን አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ማንነት ተኮር ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያን በማውገዝ ነው ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓም በህሊና ፀሎት፣በሻማ ማብራትና በውይይት እያሰበ የሚገኘው። በተያያዘም ህግ በማስከበር ግዳጅ ላይ ሆነው ውድ ህይወታቸውን እየከፈሉ በድል በመገስገስ ላይ ላሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ፣ሚሊሻና የመከላከያ ሰራዊትም ያላቸውን አክብሮት ገልፀው ጀግኖችንም አብረው እያሰቡ ነው። የባልደራስ መኢአድ ም/ቤትም በንፁሀን ወገኖች ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተፈፀመውን የዘር ፍጅት እንደሚያወግዘው ገልጧል። ለትግሉ ከባድ መስዋዕትነት የከፈሉት የእነ ፕ/ር አስራት ወልደየስና ኢ/ር ኃይሉ ሻወል ፎቶ በትልቁ መጠን ተዘጋጅቶ በግድግዳ ላይ ተቀምጧል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው የመኢአድ ዋና ጽ/ቤት አዳራሽ ተገኝቶ የመታሰቢያ ዝግጅቱን እየተከታተለ ስለሆነ ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply