የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዝደንት የሚለዬው ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ም…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዝደንት የሚለዬው ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ከ780 በላይ የጉባኤ አባላትን አዲስ አበባ ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ዋና ጽ/ቤቱ እንዲገኙ በማድረግ 9ነኛ መደበኛ ጉባኤውን ሚያዝያ 9/2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በማካሄድ ላይ ነው። በጉባኤውም:_ አቶ ማሙሸት አማረ፣ አቶ አብርሃም ጌጡ እና አቶ ታጠቅ አሰፋ ለመኢአድ ፕሬዝደንትነት ተጠቁመዋል። ይሁን እንጅ አቶ ማሙሸት አማረ የዲሞክራሲን ባህል መለማመድ አለብን፤ እኔም ደክሞኛል ለዚህም እኔ በድጋሜ ከምመረጥ አቶ አብርሃም ጌጡን ምረጡ ሲሉ ተናግረዋል። ጉባኤተኛው ግን በአቶ ማሙሸት አማረ ሀሳብ አልተስማማም። አቶ ማሙሸት ድርጅቱን እየመሩ ዲሞክራሲን እንዲያለማምዱን ለቀጣይ ሶስት ዓመት እንዲመሩን መመረጥ አለባቸው ሲል ተደምጠዋል። አቶ አብርሃም ጌጡም ጉባኤተኛው የሚሰጣቸውን ውጤት በመቀበል ድርጅቱን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሶስተኛ ሆነው የተጠቆሙት አቶ ታጠቅ አሰፋ በበኩላቸው ለታላቁ መኢአድ በሚመጥነኝ ቦታ አገልግያለሁ፤ ቀጣይም አገለግላለሁ፤ ይሁን እንጅ ለፕሬዝደንትነት አልመጥንም፤ መኢአድን ለመሸከም የሚያስችል ትክሻ የለኝም፤ ነገር ግን አቶ ማሙሸት የውጭ ህክምናቸውን አቋርጠው ስለመጡ አቶ አብርሃም ጌጡን ምረጡ በማለት በፈቃዳቸው ጥቆማውን ውድቅ አድርገዋል። የምርጫ ቦርድ አባላት ባሉበት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ ቀጥሏል። አቶ ማሙሸት በአንበሳ፣ አቶ አብርሃም ጌጡ ደግሞ በነብር ተወክለዋል። የቆጠራ ሂደት ሲጠናቀቅ ውጤቱን የምርጫ አስፈጻሚዎች ይፋ ሲያደርጉ በመኢአድ ዋና ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በሚካሄደው ጉባኤ የተገኘው አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የሚያጋራ ይሆናል። 29 ተጠቁሞ 24 የላዕላይ ም/ቤት አባላት እና 5 ተጠባባቂ አባላት ሆነው ተመርጠዋል። በተጨማሪም ለኦዲት እና ቁጥጥር 5 ተጠቁሞ 3 አባላት በጉባኤው ተመርጠዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply