You are currently viewing የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሀገርን በጋራ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ ጊዜ ወለድ ከሆነው ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመውጣት ኑ አብረን እንስራ ሲል ለተለያዩ አካላት ጥሪ አቀረበ።…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሀገርን በጋራ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ ጊዜ ወለድ ከሆነው ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመውጣት ኑ አብረን እንስራ ሲል ለተለያዩ አካላት ጥሪ አቀረበ።…

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሀገርን በጋራ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ ጊዜ ወለድ ከሆነው ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመውጣት ኑ አብረን እንስራ ሲል ለተለያዩ አካላት ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ እንደ ንስር መታደሱን በመግለጽ ኑ አብረን እንስራ ሲል ለተለያዩ ተቋማት ጥሪውን አቅርቧል። መኢአድ ላለፉት ሦስት ዓሥርት ዓመታት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለሕዝብ ነጻነትና እኩልነት እንዲሁም ለሁለንተናዊ ፍትህ በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆኖም ያላሰለሰ ትግል ሲያደርግ መቆየቱን አውስቷል። ባሳለፈው ረጅም የትግል ዓመታትም ከገዥው ፓርቲ ጀምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ነን ባዮችን ጭምር መኢአድን ለማፍረስ ያልተበጀተ በጀት እና ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም ሲል በመግለጫው አስፍሯል። ድርጅቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አልፎ ለ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ሲደርስም በእጅጉ ስለመፈተኑና ይህንም በአመራሩና በአባላቱ ትግል በተመሳሳይ በጥበብ ስለማለፉ ገልጧል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ዋና ጽ/ቤቱ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የመጡ ጋዜጠኞች ከመግለጫው ጋር በተያያዘ ላነሷቸው ጥያቄዎች የድርጅቱ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ እና ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንቱ አቶ አብርሃም ጌጡ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። መኢአድ ኑ አብረን እንስራ ሲል ጥሪ ካቀረበላቸው መካከል:_ 1) በመላ ሀገሪቱና ከአገር ውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በአገራችን ላይ እየሆነ ያለውን መጠነ ሰፊ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግር ለማስተካከል በምናደርገው ወሳኝ ትግል አብራችሁን ቁሙ። 2) አገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሚዲያዎች፣ የሚዲያ ባለቤቶችና ጋዜጠኞች መኢአድ የሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግል ለህዝቡ እንዲሰማና እንዲታይ ተደራሽ ታደርጉልን ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 3) በየደረጃው የምትገኙ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ተወካዮች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች ለህዝባችን በምናደርገው ታሪካዊ ትግል አብራችሁን ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን። 4) በየደረጃው የምትገኙ የፀጥታ አስከባሪ አካላት የሕዝባችሁን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለአገሪቱ ሉዓላዊነት የምናደርገውን ትግል ተገንዝባችሁ ሕጉ በሚፈቅደው ሁኔታ ብቻ ህዝባችሁን ታገለግሉ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 5) በየደረጃው የምትገኙ በሕዝብ አስተዳደር ላይ የተቀመጣችሁ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ህዝቡ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኝ በቅን ልቦና ሥራችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 6) በየደረጃው የምትገኙ የፍትህ አካላት ሕግና ደንብን እንዲሁም ኃላፊነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የሕዝባችንን ያላግባብ እሥርን፣ መጉላላትንና የፍትህ ጥያቄ አለማግኘትን ተረድታችሁ ሙያንና ሥነምግባርን መሠረት ባደረገ መልኩ ህዝባችሁን እንድታገለግሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 7) የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ያላችሁን ኃይማኖታዊ አስተምሮና አባታዊ ምክርን በአግባቡ ትወጡ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 😎 በንግድ የሥራ ዓለም የተሰማራችሁ ወገኖቻችን ዛሬ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ተረድታችሁ አቅምንና ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ በገበያ ላይ የሚውሉ ምርቶችን የእናንተንና የሕዝባችሁን አቅም መሠረት ባደረገ መልኩ ህዝባችሁን ታገለግሉ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 9) የአገራችን ወጣቶች ኢትዮጵያ አገራችሁ የምትገኝበትን አደገኛ ሁኔታን በመገንዘብ ጊዜ ወለድ የሆነውን ፅንፈኛ አስተሳሰብ በመፀየፍ ለእናንተና ለመጪው ትውልድ የምትሆን የጋራ አገር በትግል ለማስቀጠል በምናደርገው ትግል ዘራችሁ፣ ቋንቋችሁ፣ ኃይማኖታችሁና አካባቢያችሁ ሳያግዳችሁ አብራችሁን ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply