የመራዊ ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲሉ በከተማው በሚገኙ ፖሊሶች በመከልከላቸው ቅሬታቸውን ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ፡፡              አሻራ ሚዲያ     ጥር…

የመራዊ ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲሉ በከተማው በሚገኙ ፖሊሶች በመከልከላቸው ቅሬታቸውን ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥር…

የመራዊ ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲሉ በከተማው በሚገኙ ፖሊሶች በመከልከላቸው ቅሬታቸውን ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-09/05/13/ዓ.ም ባህርዳር ዘርን መሰረት ያደረገው የመተከሉ እልቂት እንዲቆምና ዜጎች ሰላማዊ ህይወት እንዲኖሩ የሚያሳስብ የተቃውሞ ሰልፍ በመራዊ ከተማ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ይሁን እንጅ በከተማው የሚገኝ ፖሊሶችና ከፍተኛ የስራ አመራሮች በጋራ በመሆን ሰልፉን እንደከለከሏቸው ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ በመተከል የንጹሀን ግድያ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡በዚህም የሟቾችና እና የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ ይህንን ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድገር ማሰባቸውንም ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስት ለጉዳዮ ተገቢውን ትኩረት የሰጠው አይመስልም ያሉት ወጣቶቹ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የህዝብን ድምጽ ማፈኑ ነው ብለዋል፡፡ በመተከልንና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተውን ጅምላ ጭፍጨፋ ለማውገዝ ከዚህ ቀደም የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ሰላማዊ ሰልፍ የጠራ ቢሆንም፣ በብልፅግና አመራሮች ተቋርጧል እንዲሁም አባላቶች ታስረዋል ሲሉ የመረጃ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ የከተማው የወንጀል መከላከል ሀላፊ ችሎታው አስማረ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በወጡት ነዋሪዎች ላይ ርምጃ እንወስዳለን ማለታቸውንና ከፍተኛ የሆነ ዛቻ እንዳደረጉባቸውም ምንጫችን ነግረውናል፡፡ በተደጋጋሚ የጅምላ ግድያውን ለማውገዝ ብናስብም ፍቃድ ጠይቁ በሚል ሰበብ እየተከለክልን ነው ያለት ምንጫችን ፍቃድ ብንጠይቅም እድሉን እየሰጡን እይደለም ሲሉም ነግረውናል፡፡ ይሁን እንጅ በመተከልና በሌሎች አካባቢዎች የሚደረገውን የጅምላ ጭፍጨፋ ለማውገዝ በሌላ ግዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዳሰቡም ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ንጹሀን በየቦታው እየተገደሉ ዝም ብሎ ማየት የወንጀሉ ተባባሪ እንደመሆን ይቆጠራል ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply