የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን “ኢንቨስት ኦሪጅንስ” የሚል ዓለም አቀፋዊ ፎረም ሊያዘጋጅ ነው።የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/BHGx046RvB37rYcHB7BbgvjsCpEW65fLb53TwydIZzhU7__I9IwR_LtDYaimm-7IQgopsSaa8fl1ZivJK0oAgGc2Soh1IhLg2Iu5z19EoJF0-hd8qKccU9S22Y5InjcxkSAbLuTV8l5wEuFF3Sc6p8NryzbqVpDXQcGi1fXBOnRBLUFm5hG_PXe2XWsWs9xIkzcfFc32fPkdbLi1OXncNX9pcIDIPYWS7xyQbEgdq9afhUPb5sGPlFD1TOvhsYk2QcXZW_LtNN__GQbtgajPf5UPN_AUlfBGqY_XNoKgq5x3xOLTuwBbjc8Kk0GKvz4pmdLW0MB7r53E0AYB_tppeg.jpg

የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን “ኢንቨስት ኦሪጅንስ” የሚል ዓለም አቀፋዊ ፎረም ሊያዘጋጅ ነው።

የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመሳብ የሚያስችል አለምአቀፋዊ የኢንቨስትመንት ፎረም ለማዘጋጀት ማቀዱን ገልጿል።

የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ በታለሙ የመኖሪያ ቤቶች ፣የጤና ፣የሆቴል ፣የትምህርት እና የአ.ይ.ሲ.ቲ ዘርፎች ኢንቨስትመንቶችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመሳብ አዳዲስ የፕሮጀክት ሀሳቦችን መፍጠሩን የገለፁት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሌንሳ መኮንን ናቸው።

በዚህ ፎረም ከሶስት የተለያዩ ድርጅቶች ጋር ኮንትራቶችን ለመፈራረም ማሰባቸውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ከነዚህ ድርጅቶች ጋር በሚደረገው ስምምነትም በየአመቱ 2 ቢሊየን ዶላር መሳብ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
የፎረሙ አላማም በመሬት እና ይዞታ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያን ከ5ቱ አለም አቀፍ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች ተርታ ለማሰለፍ መሆኑንም አክለዋል።

በተጨማሪም እ.ኤ.አ በ2025 የኢትዮጵያን አለምአቀፋዊ ተደራሽነትን በማስፋት የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እገዛ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

ኦቪድ ግሩፕ ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጋርነት አብረው እንደሚሰሩም ተገልጿል።
2መቶ 50 በአካል እንዲሁም 5 መቶ ደግሞ በበይነ መረብ ፎረሙን ይሳታፋሉ ተብሎ እቅድ የተያዘ ሲሆን ፎረሙም በጥር አጋማሽ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply