የመርዓዊ እና አካባቢዋ ተወላጅ የዲያስፖራ አባላት ያስተላለፉት መልክት ———————————– የአማራ ሊህቃን እና የፋኖ አደረጃጀቶችን ማዋከብና ማፈን በአስ…

የመርዓዊ እና አካባቢዋ ተወላጅ የዲያስፖራ አባላት ያስተላለፉት መልክት ———————————– የአማራ ሊህቃን እና የፋኖ አደረጃጀቶችን ማዋከብና ማፈን በአስቸኳይ ይቁም! ኗሪነታችን በሰሜን አሜሪካ፤ አውሮፓ እና የተቀሩት አህጉራት ያደረግን የመርዓዊ እና አካባቢዋ ተወላጅ የሆንን የዲያስፖራ አባላት የወጣንበትን ማህበረሰብ በተለያዩ የልማት ስራዎች ተሳትፎ ስናደርግ ቆይተናል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በህግ ማስከበር ሰበብ እየተካሂያደ ያለውን የአማራ ሊህቃን፤ ወገንትኝነታቸውን ለህዝብ ያደረጉ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት እና አመራሮችን፤ የአማራ ፈኖ፤ የሚዲያ ባለሞያዎች እና የሲቪክ ማህበራትን በጅምላ የማዋከብና የማፈን ተግባር የአማራ ማህበረሰብን መሪ አልባ በማድረግ ከዚያም ከዚህም ለሚቃጣበት ጥቃት በቀላሉ ተጠቂ እንዲሆን ምች ሁኔታ የመፍጠር እርምጃ እንደሆነ እንገነዘባለን። መንግስት እያካሂያደ ያለውን ህጋዊ አሰራርን የጣሰ የዘመቻ እስር እና አፈና ተግባር በማቆም እና እስካሁን ያፈናቸውን በአፋጣኝ እዲለቅ ስንል በአፅኖት እንጠይቃለን። በወንጃል የሚፈለጉ ግለሰቦች ካሉ ህጋዊ አሰራርን በመከተል ጉዳያቸው በፍርድ እንዲያዝ ማድረግ ሲቻል፤ ሰራዊትን በማሰማራት ዜጎችን በጅምላ የማፈን ተግባር ከጠላት እንጅ አገርን እያስተዳደርኩ ነው ከሚል መንግስታዊ አካል የሚጠበቅ አይደለም። ወደ አካባቢያችን መርዓዊ ስንመለከት ደግሞ ታጋይ ዘመነ ካሴን እና በእሱ ስር የተሰባሰቡ የፋኖ አባላትን ለማፈን በተደረገው ህገ-ወጥ እርምጃ ምክንያት በንፁሃን ላይ የደረሰውን የህይዎት መጥፋት ክስተት እናገኛለን። በዚህ አጋጣሚ ለሟች ቤተሰቦች እና ዘመዶች መፅናናትን እየተመኘን፤ ሃዘናችሁ የሁላችንም ሃዘን መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን:: ታግይ ዘመነ ካሴ ህውሃት ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት 7 በመቀላቀል አስከፊውን ስርዓት ሲታገል የነበረ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የአማራ ህዝባዊ ሃይልን በማደራጀት እና በመምራት ህውሃት በአማራ ህዝብ ላይ ሰንዝሮት የነበረውን መጠነ ሰፊ ወረራ ለመመከት የበኩሉን አስተዋፅዖ ያበረከተ ወንድማችን ነው። ታጋይ ዘመነን ለማፈን የተሰማራው ሰራዊት ዛሬም ድረስ አካባቢውን ለቆ እንዳልወጣ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። ዘመነም ሆነ በእሱ ስር የተሰባሰበ ማንኛውም ግለሰብ ፈፅሞታል የሚባል ወንጀል ካለ ጉዳዩ ህጋዊ ስርዓትን በተከተለ መንገድ በፍርድ ቤት በኩል መታየት ይገባዋል። ከዚያ ውጭ ግን ሰራዊትን አሰማርቶ ለመደምሰስ ወይም ለማፈን የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ህገ-ወጥ እና ፀረ-ህዝብ ተግባር ነው። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ ተሳትፎ እያደረጋችሁ ያላችን የመርዓዊ እና አካባቢዋ የፀጥታ አካላት እና የሲቪል አስተዳደር አባላት በሙሉ ከዚህ ታሪክ ይቅር የማይለው ተግባር እንድትታቀቡ እያሳሰብን፤ ጉዳዩን የአካባቢያችን ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በማሳተፍ በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲበጅለት የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ስንል ወገናዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በታጋይ ዘመነ ካሴም ይሁን በሌላ ግለሰብ ላይ የህይዎት መጥፋት ሆነ የአካል መጉድል አደጋ ቢፈጠር የወንጀሉ ቀጥተኛ ፈፃሚዎች ወይም ተባባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ የሚሰፍር መሆኑን እንድትገነዘቡት እያሳሰብን፤ ለፍርድ የምትቀርቡበት ቀንም እሩቅ እንደማይሆን ልንጠቁማችሁ እንወዳለን። በዚህ አጋጣሚ በአማራ ሊህቃን፤ የፋኖ አባላት እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች ላይ እየተካሂያደ ያለውን ህገ-ወጥ የአፈና ተግባር ህግ የማስከበር እርምጃ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ መንግስት ስህተቱን እንዳያርም፤ ከዚያ ይልቅ የአፈና ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሞራል ድጋፍ እያደረጋችሁ ያላችሁ የሚዲያ ሰዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ከዚህ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ ስንል ወገናዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። የመርዓዊ እና አካባቢዋ ተወላጅ የዲያስፖራ አባላት ግንቦት 20 2014 ዓም #መርዓዊ #አማራ #ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply