‹የመሰረተ ልማት ዝርፊያ አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት ለህብረተሰቡ ማድረስ እንዳንችል ፈተና ሆኖብናል›› የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ድርጅትየኤሌክትሪክ አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት…

‹የመሰረተ ልማት ዝርፊያ አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት ለህብረተሰቡ ማድረስ እንዳንችል ፈተና ሆኖብናል›› የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ድርጅት

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መላኩ ታየ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በአገራችን አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ለማዳርስ በተለይም መጭዉን የአዲስ አመት በአል ምክኒያት በማድረግ ሃይል መቆራረጥ እንዳይኖር 24 ሰአት በሚሰራ ቡድን ተዋቅረን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ሃላፊዉ አሁን ያለዉ የደምበኞች የሃይል አጠቃቀም እጅጉን እየሰፋና እያደገ መምጣቱ ጋር ተያይዞ ነባሩ ኔትዎርክ የሚፈለገዉን ያህል አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል ፡፡

ለሃይል መቆራረጡ እንደምክኒያት ያነሱት የኔትወርኩ ማርጀት ፤ በመንገድ ትራፊክ የሚደርስ አደጋ፤ የመሰረተ ልማት ስርቆትና የመንገዶች ባለስልጣን ለመሰረተ ልማት ግምባታ በሚል በሚፈርሱ መንገዶች ምክንያት የሚነኩ ገመዶች የሃይል መቆራረጥ ያስከትላሉ ብለዋል፡፡

አቶ መላኩ በነዚህ ምክኒያቶች የሚፈጠረዉን የሃይል መቆራረጥ ለመጠገን በተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል በፈረቃ ለማቋረጥ እንገደዳለን ፤ ለደረሱትም ጉዳቶች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋ በጋራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉም አንስተዋል፡፡

በተለይም በበአላት ወቅት ህብረተሰቡ ቤቱን ለማስጌጥ እና ከፍተኛ የሀይል ፍጆታ ያላቸዉን የኤሌክትሪክ መገልገያዎችን ስለሚጠቀም ነባር በሆነዉ ኔትወርክ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ ስለሚያጋጥ ማህበረሰቡ የሃይል አቅርቦትን ያገናዘበ ሃይል ቆጣቢ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ከበአሉ በፊት የሃይል መጨናነቅ እንዳያጋጥም የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ያለሰልፍ በዘረጋናቸዉ ዘመናዊ የክፍያ ስርአት እንደ ፖስ ማሽን፤ ሞባይል ባንኪንግ በመሳሰሉት አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply