
የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ህብረተሰቡ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የተከለከሉ ነገሮችን በፍጹም መያዝ እንደሌለበትና ለሚኖሩ ፍተሻዎች መተባበር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በየአካባቢው የሚደመሩ ደመራዎችም አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ፣ ከዚህ በፊት ደመራ ተደምሮባቸው የማያውቁ ቦታዎች የጸብ መነሻ እንዳይሆኑ የድሮዎቹን መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በበዓላቱ ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም ክልል መሆኑንም የተናገሩት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ፤ ክልከላው የተደረገው ርችትን ሽፋን በማድረግ ህገወጦች ህገወጥ የጦር መሳሪያቸውን የሚሞክሩበት እድል እንዳይፈጥር በማሰብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ይህንን በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብም ሆነ ተቋም በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post