
የመስከረም አበራ ቀን! ዛሬ የእናቶች ቀን ነው። የእናትነት ትርጉም የሰው ልጆችን በጋራ እንዲግባቡ በማድረግ ተስተካካይ ያለው አይመስለኝም። ይህ ቀን የገዥዎች ፍራቻ ወለደ እስር የእናትነት ቀኗን ከሁለት ልጆቿ ጋር ማሳለፍ እንዳትችል ላደረጋት እና ቀኑን በአምባገነኖች ማጎሪያ ቤት ሆና እንድታሳልፍ ለተደረገችው መስከረም አበራ መታስቢያ ይሁን። መስከረም ላለፉት አመታት ፋሽዝምንና ባህሪውን በፅናት ስትታገል ኖራለች። በዚህ ፅናቷ ምክንያት በአራስነት ጊዜዋ ሳይቀር ለተደጋጋሚ እስር ተዳርጋለች። አምባገነን ገዥዎች አምርረው የሚታገሏቸውን የመስከረም አበራ አይነት ብርቱዎችን በእስርና ተደጋጋሚ እንግልት ከመንገዳችን ዘወር እናደርጋለን ብለው ቢያምኑም የገጠማቸው ግን በተቃራኒው ነው። የበለጠ ብርታት! ኦህዴድ መራሹ መንግሥት ስልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተፈፀመ የግፍ አይነት የለም። በተለይ ደግሞ አማራን target ያደረጉ መንግሥት መራሽ ጥቃቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ንፁሃንን ህይወት ቀጥፈዋል። ወገኖቻችን በጅምላ ተገድለው ሀይማኖታዊ ፀሎት እንኳን ሳይደረግላቸው በጅምላ ተቀብረዋል። ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀም መስከረም ከፊት ሆና የግፉአን ጠበቃ የጨካኞች ተቃዋሚ በመሆን ታግላለች። በዚህም ምክንያት በደረሰባት ተደጋጋሚ እስር የእናትነት ሀላፊነቷንና ተፈጥሯዊ ፀጋዋን መስዕዋት አድርጋለች። አማራ አምርረው በሚጠሉት የትግሬ ጦረኞች መጠነ ሰፊ ወረራ ሲፈፀምበት ለአማራው እንታገላለን የሚሉ አካላት ገሚሱ ገለልተኛ ተመልካች ሲሆን ገሚሱ አማራ ራሱን እንዳይከላከል በራሱ ህዝብ ላይ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ መስኪ ግን ለህዝብ Cause ታማኝ ሆና አማራ ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን ተጠቅሞ ራሱን ከጠላት ወረራ መከላከል እንዳለበት አጥብቃ ስትሞግት ነበር። ፖለቲካን የኑሮ መደጎሚያ እና ጎጆ መውጫ አድርገው ገሸሽ የሚሉ በበዙበት ዘመን መስከረም አበራ በፅናትና በብርታት ለህዝብ መስዕዋትነት ስትከፍል ኖራለች። ስለ እውነትና ፍትህ ስትል ከጨቅላ ልጆቿ ተነጥላ፣ የእናትነት ፀጋዋን የሚፈልጉ ልጆቿን ጊዜ ሰውታ ስለግፉአን ስትል ውድ ዋጋን እየከፈለች ትገኛለች። ልክ እንደ እናት። ይህ ቀን የመስከረም አበራ ነው ! © ጥላሁን ፅጌ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post