የመስከረም 11 የሽብርተኝነት ጥቃት ተጠርጣሪዎች መዝገብ መታየት ጀመረ

https://gdb.voanews.com/4B43A33F-92EE-4067-8EED-3BE2E2335050_w800_h450.jpg

እኤአ በ2011 የመስከረም 11ዱን የሽብርተኝነት ጥቃት በማቀድና በመተባበር ተሳትፈዋል በሚል በዩናይትድ ስቴትስ በተከሰሱ 5 ተጠርጣሪዎችን ክስ አስመልክቶ የሚደረገው ችሎት በኮቪድ-19 ወረርሽ ለአንድ ዓመት ተኩል መታየት ካቆመ በኋላ ዛሬ ማክሰኞ የቅድመ ፍርድ ሂደት ሀሳብን ማድመጥ ተጀምሯል፡፡

አልቃይዳ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት የነበረው ካኻሊድ ሼክ መሀመድ እና ጥቃቱን በግንባር ቀደምትነት ያስተባበሩት ግብረ አብሮቹ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሠፈር በሆነው ጓንታናሞ ቤይ ከወታደራዊው ችሎት ይቀርባሉ፡፡

የተመሰረተባቸው ክስ ሰላማዊ ዜጎችን ማጥቃት፣ መግደል፣ አውሮፕላን መጥለፍና ሽብርተኝነት ሲሆን፣ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከሞት በሚያደርስ ቅጣት ሊቀጡ ይችላሉ፡፡

በከሳሾችና በተከላካይ ጠበቆች መካከል ምን ዓይነት ማስረጃዎችን መጠቀም እንደሚገባ አለመግባባት መኖሩም ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply