የመብራት አገልግሎት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል እንዲከናወን ሊደረግ ነው፡፡ከሐምሌ ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ…

የመብራት አገልግሎት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል እንዲከናወን ሊደረግ ነው፡፡

ከሐምሌ ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳለው በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ የድህረ መብራት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ይሆናል፡፡

እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆን ተገልጋይ የድህረ ክፍያ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ የሚከፍል ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል እንዲከፍሉ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ለኢፕድ ገልጸዋል።

በቀጣይም በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎች ከተያዘው ዓመት ሐምሌ አንድ ጀምሮ ድህረ ክፍያ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ እንዲያደርጉ ይደረጋል ያሉት መላኩ፤ አብዛኞቹ ደንበኞች የድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎቱን ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ ከአማራጮቹ መካከልም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመሆን ያስጀመረው በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ ዳይሬክት ዴቢት እንዲሁም ቴሌ ብር ዋንኞቹ ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት ደንበኞች የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች (በሞባይል ባንኪንክ፣ በሲቢኢ ብር እና ቴሌ ብር) በመጠቀም ክፍያ መፈጸም እንደሚችሉም አገልግሎቱ ገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በካርድ የማይጠቀሙ ደንበኞች (ምንም ዓይነት የቆጣሪ አንባቢ ሳይላክ ክፍያውን መክፈል የሚያስችል) ስማርት ቆጣሪ መጠቀም እንዲችሉ እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply