የመተከሉ ስብሰባ (የአሻራ ትዝብት) አሻራ ሚዲያ ታህሳስ13/2013ዓ•ም ባህርዳር የለውጡ ሀይል ተብሎ የሚጠራው የብልፅግና ስብስብ ችግርን…

የመተከሉ ስብሰባ (የአሻራ ትዝብት) አሻራ ሚዲያ ታህሳስ13/2013ዓ•ም ባህርዳር የለውጡ ሀይል ተብሎ የሚጠራው የብልፅግና ስብስብ ችግርን ቀድሞ ተንትኖ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ችግሩ ውድመት ካስከተለ በኃላ መፍትሄ የመፈለግ ልማድ አለው፡፡ በሰሜን ህወኃት የመከላከያ ሀይልን እስከሚያጠቃ ብልፅግና መፍትሄ ቀድሞ አልሰራም ነበር፡፡ በመተከልም ኢህአዴግ ብልፅግና እስከሆነበት ድረስ 60 ሺ የሚደርሱ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡ በሺዎች ተገለዋል፡፡ መተከል የጦር ቀና ሆኗል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ብልፅግና ከሽንገላ መግለጫ ውጭ ያመጣው ምንም አይነት መፍትሄ የለም፡፡ አሁን የመተከል ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንበር አስጊ ሲሆን አብይ አህመድ ከተከታዮቻቸው ጋር ወደ መተከል ወርደው ነበር፡፡ ስብሰባውም ገዳ…ዮችን የሚያበረታታ እና ተገዳዮችን የሚኮንን እንደነበር ከስብሰባው ተሳታፊዎች መረዳት ችለናል፡፡ አፈናቃዮ ተፈናቃይ፣ ገዳዮ ተገዳይ ሆኖ የቀረበበት የመተከሉ ጉባዔ ምንም ረብ የለሽ እንደነበር እና ለመፍትሄም ሩቅ እንደሆነ ተገልጧል ፡፡ ጠቅላይሚኒስትሩ ውዳሴ ወዳጅ በመሆናቸው ስራቸው ሁሉ “ለብ ለብ” መሆኑ ሀገሪቱን ያስከፍላታል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የመተከሉ ጉባዔም ከገዳይ ጋር ቁሞ ገዳይን እንደመፈለግ ያለ የሞኝ ስብሰባ ነበር፡፡ ስብሰባው እየተደረገም በድባጤ ግድያ እና ተኩስ እንደነበር ተሰምቷል፡፡ አብይ አህመድ ተራ ምክር ለግሰው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን፣ መተከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰበሰቡም አልሰበሰቡም የጦር ቀጠና መሆኑ የሚቀር አይመስልም የሚሉት ብዙዎች ናቸው፡፡ በአማራ ብልፅግና በኩል ያሉ ተግባር አልባ መግለጫዎችም ወደ ሚጨበጥ መፍትሄ ማምራት አለባቸው፡፡ ያ ካልሆነ መተከል የእርስ በእርስ ጦርነት የመጀመሪያው መጨረሻ ይሆናል፡፡ መተከል የብዙ ፍላጎቶች ግጭት የንፅሃንን ሞት መስዕዋትነት እየጠየቀ ነው፡፡ በመተከል ያለው አንዳንድ አመራርም ቀስት እያመረተ ለጭፍጨፋ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የአይን እማኞች ይገልጻሉ፡፡ ጠቅላይሚኒስትሩም ከቀስት አምራቾች ጋር ተሰብስበው መፍትሄ ለማምጣት ሞክረዋል፡፡ ግን ፈፅሞ ሊሳካ የሚችል አይመስልም፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply