የመተከሉ እልቂት እንዲቆም የሚያሳስብ የተቃውሞ ሰልፍ ነገ በመራዊ ከተማ ይደረጋል፡፡ ( አሻራ ጥር 8፣ 2013 ዓ.ም)  የመተከል ቀውስ ያለማቋረጥ ቀጥሏል፡፡ የሟቹ እና የተፈናቃዮ ቁጥር እ…

የመተከሉ እልቂት እንዲቆም የሚያሳስብ የተቃውሞ ሰልፍ ነገ በመራዊ ከተማ ይደረጋል፡፡ ( አሻራ ጥር 8፣ 2013 ዓ.ም) የመተከል ቀውስ ያለማቋረጥ ቀጥሏል፡፡ የሟቹ እና የተፈናቃዮ ቁጥር እ…

የመተከሉ እልቂት እንዲቆም የሚያሳስብ የተቃውሞ ሰልፍ ነገ በመራዊ ከተማ ይደረጋል፡፡ ( አሻራ ጥር 8፣ 2013 ዓ.ም) የመተከል ቀውስ ያለማቋረጥ ቀጥሏል፡፡ የሟቹ እና የተፈናቃዮ ቁጥር እያደር እየጨመረ ነው፡፡ መንግስትም ለጉዳዮ ተገቢውን ትኩረት የሰጠው አይመስልም፡፡ የመተከልን እና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተውን ጅምላ ጭፍጨፋ ለማውገዝ ከዚህ ቀደም አብን ሰልፍ የጠራ ቢሆንም፣ በብልፅግና አመራሮች ተቋርጧል፡፡ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ግዛቸው ሰልፍ የወጣ እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸውም በወቅቱ አነጋጋሪ ሆኖ አልፏል፡፡ የአማራ ወጣቶች በተደጋጋሚ የጅምላ ግድያውን በማውገዝ ሰልፉ ቢጠሩም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ የመራዊ ወጣቶች ነገ በመተከል የተደረገውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለማውገዝ ቀጠሮ እንደያዙ አሻራ ሰምቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply