የመተከል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከመተከል ተፈናቅለው ቻግኒ(ራንች) ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ሰጠ።      (አሻራ  ታህሳስ 26፣  2013 ዓ.ም ) ከመተከል ዞን ሰባት (…

የመተከል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከመተከል ተፈናቅለው ቻግኒ(ራንች) ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ሰጠ። (አሻራ ታህሳስ 26፣ 2013 ዓ.ም ) ከመተከል ዞን ሰባት (…

የመተከል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከመተከል ተፈናቅለው ቻግኒ(ራንች) ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ሰጠ። (አሻራ ታህሳስ 26፣ 2013 ዓ.ም ) ከመተከል ዞን ሰባት (7)ወረዳዎች በጉምዝ ታጣቂዎች ግድያ ዘረፋ እና ድብደባ የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ነብሳቸውን ለማትረፍ ወደ አማራ ክልል ከገቡ 44,000 አማራ እና አገው መካከል ለ1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ) አቅመ ደካሞች ፣ነብሰ ጡሮች እና አጥቢ እናቶች የአንድ ሚሊዮን(1,000,000) ብር ግምት ያለው ድጋፍ አድርጓል። እርዳታው የተሰበሰበው :- > ከመተከል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት > ከምዕራብ አውስትራሊያ አማራ ሴቶች ማህበር > ከካናዳ አማራ ህብረት > ከደቡብ አውስትራሊያ አማራ ማህበር > ከአገር ውስጥ የተለያዩ ግለሰቦች ሲሆን እርዳታውን ለተፈናቃዮች ለማድረስ የወጣት ማህበር ተወካዮች፣የቻግኒ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎ፣የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ግዥና ፋይናንስ ክፍል እና ግለሰቦች ተካፍለዋል ያሉት የመተከል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተወካይ ዶ/ር በቃሉ ታረቀኝ ለአንድ ሺ አምስት መቶ ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪግ ዱቄት ፣ሳሙና እና ጨው ማድረስ ችለናል ብለዋል። ዶ/ር በቃሉ ታረቀኝ እንደገለፁት ይሄ እርዳታ ለኮሚቴው የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ወደመደበኛ ህይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ ድረስ ይሄን የሰባዊ እርዳታ አጠናክረን እንቀጥላለንም ሲሉ ገልፀውልናል።በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ያሉ ወገኖቻችንም ለተፈናቃዮች እርዳታ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ተፈናቃዮችን በተገቢው መልኩ ለማገዝ በመንግስት በኩል ክፍተት አለ ያሉት ዶ/ር በቃሉ ተፈናቃዮቹ ያረፉበት ቦታ ጫካ ውስጥ በመሆኑ ከተፈናቃዮች ጋር ለመገናኘት እና እርዳታውን ለማከፋፈል ፈታኝ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።በመጨረሻም እርዳታውን በማከፋፈል ስኬታማ እንድንሆን ላገዙን የአማራ ልዩሐይል ፣የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ፣የቻግኒ ከተማ ፀጥታ ቢሮ እና የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎችን አመስግነዋል። ሙሉ የእርዳታውን አሰባሰብ እና ስርጭት በተመለከተ በአሻራ ሚዲያ ይዘን የምንቀርብ መሆኑን እንገልፃለን !!

Source: Link to the Post

Leave a Reply