የመተከል ተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪ

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጥቃት ደርሶባቸው የተፈናቀሉና በመጠለያ ያሉ ዜጎች አሁንም የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገለፁ።

ኦነግ ሸኔ የተሰኘው ታጣቂ ቡድን ፈጽሞብናል ባሉት ጥቃት በርካታ ዜጎች መፈናቀላቸውን የገለፁት የጥቃት ሰለባዎቹ፤ የሰብኣዊ እርዳታ አለማግኘታቸውንም አሳውቀዋል።

በዞኑ የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት በአካባቢው ሰላም ለማምጣት እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው፤ ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር እያዋልኩ ነው ብሏል።

የመንግሥት ባለሥልጣናት ቁርጠኝነት መጓደል በመተከል ዞን የተፈጠረው የሰላም ዕጦት በተፈለገው ፍጥነት እንዳይረጋጋ አድርጓል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ምክትል ኃላፊው ሙሳ አህመድ መውቀሳቸው ይታወሳል።

ቀጣናው የደኅንነት ስጋት ከተጋረጠባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች መካከል ፊት ተጠቃሽ ሆኖ ሲቀጥል፤ መንግሥት በስፍራው ያለውን የፀጥታ ስጋት ለመቅረፍ ቁርጠኛ ነኝ እያለ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply