የመተከል  አዳር (ታህሳስ 17፣2013 ዓ.ም ባህርዳር) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  በቡለን ወረዳ የደረሰውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ተጨማሪ ሀይል ወደ መተከል ይገባል ቢሉም፣ ተጨማሪ ሀይሉ እ…

የመተከል አዳር (ታህሳስ 17፣2013 ዓ.ም ባህርዳር) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቡለን ወረዳ የደረሰውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ተጨማሪ ሀይል ወደ መተከል ይገባል ቢሉም፣ ተጨማሪ ሀይሉ እ…

የመተከል አዳር (ታህሳስ 17፣2013 ዓ.ም ባህርዳር) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቡለን ወረዳ የደረሰውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ተጨማሪ ሀይል ወደ መተከል ይገባል ቢሉም፣ ተጨማሪ ሀይሉ እንዳልደረሰ በጉባ እና በድባጤ ያሉ ነዎሪዎች አረጋግጠዋል፡፡ በጉባ እና በድባጤ ምሽቱን ስጋት የነበረ ሲሆን፣ የከፋ ጉዳት አልደረሰም፡፡ የመከላከያ ሀይል ግን የተባለውን ያህል በአካባቢው የለም፡፡ በሌላ በኩል በቡለን ወረዳ የሟቾች ቁጥር 300 ሊደርስ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን፣80 ሰዎች በፀና ቆስለው ቡለን ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ቡለን ወረዳ ብቻ 50 ሺ ተፈናቃይ የተመዘገበ ሲሆን፣በጓንጓ ወረዳ መንታውሃ ቀበሌ ደግሞ የተፈናቃዮች ቁጥር 60 እየደረሰ ነው፡፡ በዳንጉር፣በጉባ፣በድባጤ ባሉ ቀበሌዎች የተፈናቀሉት ቁጥር ደግሞ ከ40 ሺ በላይ ደርሷል፡፡ በድምሩ በሁለ…ት ሳምንታት ብቻ ከ150 ሺ ሰው በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠያቂ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል በመተከል የመንግስት መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ ስለሆነ፣ ለረጂዎች ምግብ ለማድረስም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የመንግስት መዋቅሩ እየፈራረሰ የታጣቂዎች ምሽግ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም እንዳረጋገጠው በመተከል ላይ ዘር ተኮር ግድያ የቢሻንጉል ጉምዝ አመራሮች ዋና ተዋናይ እንደሆኑ አረጋግጧል፡፡ በአካባቢው የተሰማራው ወታደርም አቅመ ቢስ ሆኖ የንፁሃንን ሞት ማዳን እንዳልቻለ እንባ ጠባቂ ተቋሙ አረጋግጧል፡፡ የብልፅግና አመራሮችም በጅምላ ግድያው እጃቸው እንዳለበት ተቋሙ ባወጣው ጥናት መረዳት ችሏል፡፡ ታዋቂው ፖለቲከኛ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሀገሪቱ ውስብስብ ችግር መንስዔ ዓላማ ቢሱ ብልፅግና መሩ መንግስት ነው ሲሉ ለአሻራ ተናግረው ነበር፡፡ የአውሮፓ ህብረትም ትናንትና ምሽት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል ብሏል፡፡ በመተከል የደረሰውን ጅምላ ጭፍጨፋም ያወገዘ ሲሆን፣አካታች እና አሳታፊ ውይይቶች ያስፈልጋሉ ሲልም መክሯል፡፡ በሌላ በኩል ትናንትና የገቡት ወታደራዊ አመራሮች ከአሻድሌ ሀሰን ካድሬ ጋር ውይይት ያደረገ ቢሆንም፣ከገዳይ ጋር ቁሞ ግድያን ማቆም ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ልክ እንደ መተከሉ ሁሉ በደቡብ ኢትዮጵያ በኮንሶ ዞን 60 ሰዎች ሲገደሉ፣60 ሺ ሰዎች ደግሞ በግፍ ተፈናቅለዋል፡፡ በወለጋም ግድያ እና መፈናቀሉ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ከዚህ ቀደም ከዚህ ሁሉ ግድያ ጀርባ ህወኃት አለበት ይባል ነበር፡፡ ነገር ግን ህወኃት ሲከስምም ግድያው ተጠናክሮ መቀጠሉ ብልፅግና ከህወሓት የባሰ መንግስታዊ አሸባሪ እንደሆነ አረጋጋጭ ነው እየተባለ ነው፡፡ በአማራ እና በኦሮሞ ብልፅግናዎች መካከል የተካረረ መቃቃር እየተፈጠረ ሲሆን፣በቅርቡ በባህርዳር “የኦሮማራ ” መድረክም እንደሚካሄድ አሻራ ሰምቷል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ችግር በስብሰባ አዳራሽ ሳይሆን በህግ እና ስራዓት የሚፈታ ስለሆነ ውይይቱ ፍሬ ቢስ እንደሚሆን ከወዲሁ ቅድመ ግምት ተይዟል፡፡ የኦሮሚያ ብልፅግና በሀረር፣በአዲስአበባ፣በድሬድዋ፣በኮንሶ ፣በመተከል፣በደቡብ መፈረካከስ እና ቀውስ እጅ እንዳለበት በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡ ብልፅግና ግልፅ ፍኖተ ካርታ እና ዓላማ የሌለው “የኩታሮች ማህበር” እና “የተረት አውሪዎች” ስብስብ በመሆኑ ብልፅግና ህግ እና ስራዓት ሊያረጋግጥ አለመቻሉንም የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡ የማታ የማታ ብልፅግና ተበሳብሶ ሀገሪቱ ወደ ሽግግር መንግስት መሄዷም የሚቀር አይመስልም የሚሉት ተንታኞች፣ ብልፅግና የ2013ን ምርጫ እንኳን የማስኬድ አቅም የለውም ይላሉ፡፡ ብልፅግና በሚዲያ የሚናገረው እና የሚተገብረው ፍፁም የተለያ በመሆኑ ህዝቡ ራሱን አደራጅቶ እና ተናቦ ህልውናውን እንዲያስቀጥል ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply