የመተከል እና የወለጋ ግርዶሾች፣          አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ 7/2013ዓ•ም ባህርዳር ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ መቀሌ ሆነው በሰጡት መግለጫ  ከህወሓት መ…

የመተከል እና የወለጋ ግርዶሾች፣ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 7/2013ዓ•ም ባህርዳር ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ መቀሌ ሆነው በሰጡት መግለጫ ከህወሓት መ…

የመተከል እና የወለጋ ግርዶሾች፣ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 7/2013ዓ•ም ባህርዳር ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ መቀሌ ሆነው በሰጡት መግለጫ ከህወሓት መጥፋት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኗል ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን በመተከል እና በወለጋ ንፅሃን እየታረዱ እና እየተፈናቀሉ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በመተከል ያለው የወታደር ስምሪት ሰላምን ሊያረጋግጥ አለመቻሉ የንፁሃንን ሞት እንዲፋጠን አድርጎታል፡፡ በየዕለቱ ለሽፋን የሚሰጠው ሽፍቶች ተደመሰሱ የሚለው መግለጫ ከመግለጫ ያላለፈ እንደሆነ በየቀኑ የሚፈናቀሉ ዜጎች ምስክር ናቸው፡፡ በተመሳሳይ በወለጋም ንፅሃን እየታረዱ እና እየተፈናቀሉ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ኦሮሚያ ሰላም ነው፡፡ ወደ ልማት ዙረናል የሚል ይዘት ያለው መግለጫ አውጥቷል፡፡ የቢሻንጉል ጉምዝ ብልፅግናን የአማራ ብልፅግናን የአሮጌ ስራዓት ናፋቂ ብሎ መወረፉ ይታወሳል፡፡ ብልፅግና ህወኃትን ለስልጣኑ እንጂ ለህዝብ ተጠቃሚነት ብሎ እንዳላጠፋው የሰሞኑ ሁኔታዎች አመላካች ሲሆኑ፣ በተለይ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና የህገመንግሥቱ ጠበቃ ነኝ ሲል በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡ ስለዚህ በሀገሪቱ ያለው ህግ እና ስራዓት የህወሓት ሆኖ እንደሚቀጥል ከብልፅግና የሚወጡ መግለጫዎች ያሳያሉ፡፡ ውህድ ሀገራዊ ፓርቲ ነኝ የሚለው ብልፅግና እርስ በእርሱ እየተወራረፈ እና እየተዘላለፈ፣በንፁሃን ዜጎች ላይ ሞት ፈርዷል፡፡ በመተከል ብልፅግና ከተመሰረተ ወዲህ ከ60 ሺ በላይ አማራዎች፣ሺናሻዎች እና አገዎች እንደተፈናቀሉ የታወቀ ሲሆን፣ ለዚህም ሁነኛ መፍትሄ ሳይሰጠው ዘልቋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቢሻንጉልን 37% ወደ ኦሮሞነት የጠቀለልነው ሲሆን፣በቀጣይም ሀረርን እና ጋምቤላን ለመጠቅለል እንሰራለን ማለታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ያሶ አይነት ወረዳዎች ከቢሻንጉል ወጥተው ወደ ኦሮሚያ ሲሄዱ እና ቢሻንጉልን የኦሮሚያ እናደርጋለን ሲባል የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ምን አይነት መግለጫ አላወጣም ነበር፡፡ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የብልፅግና ዓላማ ኢትዮጵያን የኦሮሞ ማድረግ ሲሆን፣ ለዚህም አማራን በማዳከም ሌሎች ብሄረሰቦችን የኛ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ የብልፅግና ፖለቲካ ቁማር ነው የሚሉት አቶ ሽመልስ ቁማሩን ደግሞ አሳምነንም አወዛግበንም (convenience and confusion ) እየበላነው ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አሁንም ብልፅግና ከሰሜን ተጠራርጎ የደቡብ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ እንሰራለን የሚል አስተያየት እየወጣ ሲሆን፣በጥቅሉ እንደ አሻራ መረዳት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገና ከህመሙ ለማገገም ብዙ ይቀረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply