‹‹የመንግሥት ፕሮጀክቶች መጎተት ሳቢያ ከ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ተከስቶል! የ34 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ፀድቆል! ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
‹‹የመንግሥት ፕሮጀክቶች መጎተት ሳቢያ ከ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ተከስቶል! የ34 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ፀድቆል!
ሚሊዮን ዘአማኑኤል

የህወሓት/ኢህአዴግ የመለሰ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው መንግሥት መር ልማታዊ መንግሥት በኦህዴድ/ኢህአዴግ ዘመንም ቀጥሎል!!!
አሻንጉሊት የኢትዮጵያ ባንኮች፣ ከህወሓት ወደ ኦህዴድ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ዘመን ተሸጋግሮል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም ባንክና የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የውጭ ብድር መበደር ታግዶል፡፡ በዚህም የተነሳ፣ ኦህዴድ/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚወስደው ብድር ጨምሮል! ባንኩ ገንዘብ ያትማል!! ኦህዴድ/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወስደው ብድር ጨምሮል!
• መጋቢት 27 ቀን 2011አ/ም የኢፊዴሪ የሕዝብ ተወካች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት የ33 .9 ቢሊዮን ተጨማሪ በጀት አፀደቀ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2011 አ/ም በጀት ዓመት 33.9 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ፡፡ ተጨማሪው በጀት ክፍያቸው ላልተከፈሉ ፕሮጀክቶች ክፍያ ለመፈፀም፣ ለቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የመንገድ ግንባታና የኤሌትሪክ ዝርጋታ ወጪን ለመሸፈን፣ የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከልና ለመቆቆም እንዲሁም በበጀት አመቱ የተቀመጡ የፕሮግራም በጀት ግቦችን ለማሳካት የሚውል መሆኑ ተገልፆል፡፡ በ2011 ዓ/ም ፌዴራል መንግሥት 346 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቆ ነበር፣ ፌዴራል መንግሥት በ8 ወራቶች ውስጥ በጀቱን ጨርሶ 34 ቢሊየን ብርና ከ60 እስከ 70 ቢሊዮን ብር ከንግድ ባንክ ብድር ተበድሮል፡፡ የመንግሥት የበጀት ጭማሪውና ብድር የዋጋ ግሽበት ከሁለት አሕዝ በላይ በመሆን የህዝቡን ኑሮ ያናጋል እንላለን፡፡ የፌዴራል መንግሥት ወጪውን መቀነስና የግብርና ታክስ የመሰብሰብ አቅሙን ማጠናከር ተስኖታል እንላለን፡፡ መንግሥት በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚው ሚዛን ማስተካከል አልተቻለም፣ የአመታዊው በጀት ጉድለት የተነሳ የ34 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ፌዴራል መንግሥት ጠይቆል፡፡ የመንግሥት ወጪ ጨምሮል፡፡
• የገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት መሠረት ‹‹በተጎተተ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ሳቢያ ከ43 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አጋጥሞል›› ተብሎል፡፡ ኦህዴድ መንግሥት መር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታውን በየፈርጁ በማጠናከር ቀጥሎል፡፡ የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ መሪ ሚናውን እንዳይወጣ የኦህዴድ/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶቻቸው ኢፈርት፣ ጥረት፣ ዲንሾና ወንዶ በመላ ሃገሪቱ የንግድ መረባቸውን በመዘርጋት ልማታዊ መንግሥታቸውን በግሉ ዘርፍ ላይ ነቀላና ተከላ በማከናወን ሥራ ተጠምደዋል፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ መር የሚሆንበት ፍኖተ ካርታ አቅጣጫ አልነደፈም፡፡ የሃገሪቱ ምጣኔ ኃብት ጥናታዊ መረጃ እንሆ፡-

{1} የኦህዴድ/ኢህአዴግ በአጠቃላይ 23.1 ቢሊዮን ብር ብድር ለኦሞ ኩራዝ ስኮር ፕሮጀክቶች ‹‹ንግድ ባንክ ለፕሮጀክቱ አሥር ቢሊዮን ብር አበድሮል፡፡›› እንዲሁም ‹‹ንግድ ባንክ ለስኮር ኮርፖሬሽን ለውጭ ዕዳ መክፈያና ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ 13.1 ቢሊዮን ብር ብድር እንዲሠጥ መንግሥት ጠየቀ ››) በአጠቃላይ 23.1 ቢሊዮን ብር ብድር ይሆናል፡፡

{2} የኦህዴድ/ኢህአዴግ በአጠቃላይ 34.8 ቢሊዮን ብር የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣በመጀመሪያ በ33 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞች ቤቶች ሰርቶ ለማከራየት የሚል ዓላማ ያለው ሲሆን በመቀጠልም የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች ሊገነባቸው ላቀዳቸው አፓርታማዎችና ቪላ ቤቶች፣ 1.8 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ 34.8 ቢሊዮን ብር መንግሥት መር የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት በቤቶች ግንባታ ላይ ማድረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሽባ ያደርገዋል እንላለን፡፡ የቤቶች ግንባታ በግሉ ዘርፍ መሪነት ሊከናወን የሚችል ዘርፍ ሲሆን ኦህዴድ /ኢህአዴግ መንግሥት ከዚህ ዘርፍ የሙስና ሰንኮፉን መንቀል ግድ ይለዋል እንላለን፡፡

{3} የኦህዴድ/ኢህአዴግ 29 ቢሊዮን ብር የአዲስ አበባ ወንዞች ዳር ተፋሰስ ልማት መንግሥታዊ ፕሮጀክት፡-የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ከ50 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በ29 ቢሊዮን ብር (1.028 ቢሊዮን ዶላር) ወጭ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ከመንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ በአክሲዬን መሸጥ አለበት እንላለን፡፡

{4} የኦህዴድ/ኢህአዴግ 5.3 ቢሊዮን ብር ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ እንዲያውሉ በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልል እንዲውል ተወስኖል፡፡ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ከመንግሥታዊ ፕሮጀክት ወደ ግል ዘርፍ በአክሲዬን ለግል ባለሃብቶችና ህዝብ መሸጥ ይኖርበታል እንላለን፡፡
የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የመንግሥት ሪፎርም ፕሮግራሞች በጥንቃቄ እንዲታቀዱ አሳሳቡ 31 ማርች 2019፡-መንግሥት በፋይናንስ ዘርፍ፣ በታክስ፣ በግሉ ዘርፍ፣ በፕራይቬታይዜሽንና በሌሎችም መስኮች የሪፎርም አጀንዳዎች ሲሆኑ ተገቢው ዕቅድ በመንደፍና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዕርምጃዎች ቅድሚያውን በመሰጠት መተግበር ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል አሳስበዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ኖራ ዲሄል፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሁኔታ ከ2011 እስከ 2016 ዓ/ም ሪፖርት መሠረት በማክሮ ኢኮኖሚ ክፍልና የድህነትና የኢኮኖሚ አቅምን ከቤተሰብ ፍጆታና የኑሮ ደረጃ ጋር በማዛመድ አመላክቶል፡፡ መንግሥት በማክሮ ኢኮኖሚው መስክ በተለይም በዋጋ ግሽበትና በገንዘብ አቅርቦት መጨመር፣ በአገር ውስጥ ብድር፣ በውጭ ብድር ዕዳና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዕዳ ሁኔታ ላይ በግልፅነት ላይ የተመሠረተ አሠራር እንዲከተል ያሳሳቡት የባንኩ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ኖራ ዲሄል ናቸው፡፡…. መንግሥት የውጭ ብድር መቀነሱን ቢያስታውቅም፣ ከአገር ውስጥ ምንጮች የሚበደረው ገንዘብ መጠን ጨምሮል ያሉት የኢኮኖሚ ባለሙያዋ፣ ከዚህ ባሻገር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብድር መጠንና የብድር ሥርዓታቸው በግልፅ መታወቅ እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡ ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው 15 በመቶ ደሀው የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ መሻሻል ካለማሳየቱም በላይ፣ ፈጣኑ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትም ምንም አልጠቀመውም ብለዋል፡፡
አሻንጉሊት የኢትዮጵያ ባንኮች፣ ከህወሓት ወደ ኦህዴድ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ዘመን በፌዴራል መንግሥት በባንኮች አሠራር የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መገለጫዎች በናሙናነት እንሆ፡፡

{1} ‹‹ንግድ ባንክ ለስኮር ኮርፖሬሽን ጣና በለስ ቁጥር አንድና ኦሞ ኩራዥ ቁጥር አንድ ለውጭ ዕዳ መክፈያና ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ 13.1 ቢሊዮን ብር ብድር እንዲሠጥ መንግሥት ጠየቀ ›› የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተፈርሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በግልባጭ ደብዳቤ ፣የስኮር ልማት ሥራዎች የሚውል 5.7 ቢሊዮን ብር፣ ለብድርና ወለድ መክፈያ 7.4 ቢሊዮን ብር፣ በጠቅላላው 13.1 ቢሊዮን ብር ኢብባ የተቀመጠውን ጣሪያ የጠበቀ መሆኑ ተረጋግጦ እንዲሠጣቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ዋስትና የሰጠ መሆኑን ደብዳቤው ጠይቆል፡፡ ህወኃት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ የስኮር ልማት ኮርፖሬሽንን ወደ ግል ዘርፍ በፕራይቬታይዜሽን ፣ እንደ የአየር መንገድ፣ የኢትዮቴሌ፣ የምድር ባቡር፣ የንግድ መርከብ፣ የመብራት ኃይል፣ ወዘተ ወደ ግል ዘርፍ በፕራይቬታይዜሽን የማዘዋወር ውሳኔ ለምን ተግባራዊ አልሆነም!!!
ስኮር ኮርፖሬሽን ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ከቻይና የልማት ባንክ ላገኘው ብድር የግዴታ ክፍያና ወለድ በአጠቃላይ 4.5 ሚሊዮን ዶላር በመክፈሉ፣ ባንኩ ብድሩን በመያዙ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አምስት ስኮር ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ መቆሙን ገልፆል፡፡
{ሀ} ረብዕ መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ/ም በሪፖርተር ጋዜጣ ለኦሞ ኩራዥ ስኮር ፕሮጀክቶች ‹‹ንግድ ባንክ ለፕሮጀክቱ አሥር ቢሊዮን ብር አበድሮል፡፡››
{ለ} ሪፖርተር ጋዜጣ 3 አፕሪል 2019 እኤአ (‹‹ንግድ ባንክ ለስኮር ኮርፖሬሽን ለውጭ ዕዳ መክፈያና ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ 13.1 ቢሊዮን ብር ብድር እንዲሠጥ መንግሥት ጠየቀ ››) በአጠቃላይ 23.1 ቢሊዮን ብር ብድር ይሆናል፡፡
• ከ10 አመታት በፊት የስኮር ልማት ፕሮጀክቶች በደቡብ ክልል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን (ሰላማጎና ኛንጋቶም ወረዳዎች) በቤንች ማጂ ዞን (ሱርማና ሜኢኒት ሻሻ ወረዳዎች) እንዲሁም በካፋ ዞን (ዴቻ ወረዳ) አካባቢ ሲሆን የኦሞ ኩራዝ የስኮር ልማት ፕሮጀክቶች በመባል ይታወቃል፡፡ ፕሮጀክቱ በ100 ሽህ ሄክታር መሬት ላይ በቀን 60 ሽህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው አራት ስኮር ፋብሪካዎች እየተገነቡ ነው፡፡ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ ሦስቱ በቀን 36 ሽህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 205 ሚሊዮን ኩንታል ስኮርና በአመት 28 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኦሞ ኩራዝ የስኮር ልማት ፕሮጀክቶች፣ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስ 34.8 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ውጪ ወጥቶል፡፡
• የስኮር ኮርፐሬሽን የስኮር ልማት ፕሮጀክቶች ለማከናወን ሜቴክ 77 ቢሊዮን ብር ወስዶ ሳይሠራ ዘርፎታል፡፡ ከሜቴክ በኃላ ከእነዚህ አራት ፋብሪካዎች በቻይና ኮምፕላንት ኩባንያ የተገነቡት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለትና ሶስት ስኮር ፋብሪካ ወደ ምርት ገብተዋል፡፡ሁለቱ ፋብሪካዎች ግንባታቸው በገንዘብ ዕጦት ተቆርጦል፡፡ ውጭና አገር ውስጥ ብድር የወሰደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመጀመሪያው የእቅድና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በ2007ዓ/ም ተጠናቀው፣ የአገሪቱን የስኮር ፍላጎት በማማላት በውጭ ንግድ ገቢ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ የሚል ህልም ነበር፡፡
• የኦህዴድ/ ኢህአዴግ መንግሥት የስኮር ልማት ኮርፖሬሽን እንደ የአየር መንገድ፣ የኢትዮቴሌ፣ የምድር ባቡር፣ የንግድ መርከብ፣ የመብርት ኃይል፣ ወዘተ ወደ ግል ዘርፍ በፕራይቬታይዜሽን የማዘዋወር ውሳኔ ለምን ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ዝሆኑን ሸጦ ጭራውን ላይ ኢንቨስት ማድረግ ምን ይሉታል፡፡ ሰባቱን የስኮር ፍብሪካዎች ለውጭና ለሃገር ውስጥ ባልሃብቶች ማለትም ወደ ግሉ ዘርፍ በማዞር መሸጥና ቀሪዎቹን ሶስት ፋብሪካዎች መንግስት ስር እንዲቆዮ ማድረግ እንዲሁም የሜቴክ 77 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ማስመለስ ገንዘቡን ለወጣቶች የስራ እድል ሊፈጥሩ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን መቅረፅ አስፈላጊ ነው፡፡ ኦህዴድ/ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርገው ብድር ሀገሪቱን ኢኮኖሚ መቀመቅ ይከተዋል እንላለን፡፡ ከዚህ ይልቅ የስኮር ልማት ፋብሪካዎችን በአክሲዮን ለግል ባለኃብቶች መሸጥ ብቸኛ አማራጭ ነው እንላለን፡፡ መንግሥት በባንኮች አሠራር ላይ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መቆም አለበት፡፡

{2} ቤቶች ኮርፖሬሽን የመጀመሪያውን ግንባታ ለመጀመር የ1.8 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈራረመ ፡-የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በድሬዳዋ) ከተሞች ሊገነባቸው ላቀዳቸው አፓርታማዎችና ቪላ ቤቶች፣ በአዲስ አበባ በአምስት ሥፍራዎች በዘጠኝ ክፍላተ ከተሞች ውስጥ ከ7 እስከ 12 ፎቅ ህንፃዎች ከወለል በታች 3 ምድር ቤቶች ያላቸው ስምንት ብሎኮች ቅይጥ አገልግሎት የሚሰጡ፣ በመጀመሪያ ዙር በሁለት አመት የሚጠናቀቁ 435 የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የግንባታው ወጪ 1.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈንም ኮርፖሬሽንኑ ይፋ አደርጎል፡፡ መጋቢት 6 ቀን 2011 ዓ/ም አራት አገር በቀል ድርጅቶችና(እቴቴ ኮንስትራክሽን፣ ኤፍኤ ኮንስትራክሽንና አብርሃም ንጉሴ ኮንስትራክሽን ) አንድ የቻይና ተቆራጭ ጋር ተፈራርመዋል፡፡
መንግስት ከቤቶች ልማት ግንባታ መውጣትና ወደ ግሉ ዘርፍ ማዘዋወር ሞርጌጅ ባንክ ሥራ ማስጀመር የ10/90፣ 20/80 እና 40/60 የኮንዶሚኒየም ግንባታዎች በሞርጌጅ ባንክና በሪል ስቴት ዲቨሎፐርስ ማስጨረስ በመንግሥት ሥር የሚገኙ 17 ሽህ ቤቶች ለግሉ ዘርፍ በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገንዘቡን ለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች በሃገር አቀፍ ደረጃ በባለሙያዎች ተቀርፀው መተግበር ያስፈልጋል፡፡
የቀድሞው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ በደርግ መንግስት በአዋጅ የተወረሱ ቤቶችን እንዲያስተዳድርና አዳዲስ ቤቶችን እንዲገነባ የተቆቆቀመ ድርጅት ነበር፡፡ከ1983 ዓ/ም ወዲህ አዳዲስ ቤቶች እንዳይገነባ ፣ ያሉትን ቤቶች ብቻ እንዲያስተዳድር ተወስኖበት ነበር፡፡ ከ26 ዓመታት በሆላ ደግሞ፣በየካቲት ወር 2009 ዓ/ም እንደ አዲስ በድጋሚ የተቆቆመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን፣ በማስተር ፕላኑ ዞን 3 እና 4 ውስጥ እስከ 10 ፎቅ የሆኑ በአጠቃላይ 16 ሽህ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ አውጥቶል፡፡ ቤቶቹ ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በኪራይ ለማስተላለፍ ነው፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ዜጋ በ10/ 90፣ በ20/ 80 እና በ40/60 ቤቶች ተደራጅተው ቤት ሊገነቡ ሲገባ በህዝብ ገንዘብ በግብር ከፋዩ ደም የኪራይ ቤቶች ሊያገኙ አይገባም፡፡ የመንግስት ተሸሚዎችና፣ ለሠራተኞች በየትኛው መልካም አስተዳደር ስነምግባራቸው፣የሞራል ብቃታቸውና፣ ስብዕናቸው ነው በግብር ከፋዩ ገንዘብ ቤቶች የሚገነቡላቸው ይሄ አሠራር በመንግሥት በጀት፣ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ማድረግ የጥቅም ግጭት፣ መጠቃቀምና፣ የአድልኦ አስራርን በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞች ቤቶች ሰርቶ ለማከራየት የሚል ዓላማ ያለው ሲሆን አሁን ደግሞ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች ሊገነባቸው ላቀዳቸው አፓርታማዎችና ቪላ ቤቶች፣ 1.8 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ 34.8 ቢሊዮን ብር መንግሥት መር የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት በቤቶች ግንባታ ላይ ማድረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሽባ ያደርገዋል እንላለን፡፡ የቤቶች ግንባታ በግሉ ዘርፍ መሪነት ሊከናወን የሚችል ዘርፍ ሲሆን ኦህዴድ /ኢህአዴግ መንግሥት ከዚህ ዘርፍ የሙስና ሰንኮፉን መንቀል ግድ ይለዋል እንላለን፡፡ በባንክ ቁጠባ ፕሮግራም የተሠሩ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን የወረሰ መንግሥት በህግም በሞራልም አላዋቂ መንግሥት ነው፡፡ የባንክ ተቀባይነት በህብረተሰቡ ዘንድ እምነት አሳጥቶል፡፡ ባንክ ህወሓት/ ኦህዴድ መንግሥት ጣልቃ ገብነት እራሱን ነፃ ያውጣ እንላለን፣ አድርባና ዘረኛ የባንክ ሙያተኞች ከዘርፉ ተነቅለው ሳይወጡ ለውጥ አይመጣም፡፡ የባንክ ሙያተኞች ማህበራት ተጠናክረው በንኩን መታደግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡

{3} 29 ቢሊዮን ብር የአዲስ አበባ ወንዞች ዳር ተፋሰስ ልማት መንግሥታዊ ፕሮጀክት፡-የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ከ50 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በ29 ቢሊዮን ብር (1.028 ቢሊዮን ዶላር) ወጭ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን የካቲት 21ቀን 2019 እኤአ የቪኦኤ እስክንድር ፍሬው ዘግቦል፡፡ የቤተ-መንግሥት አካባቢ የከተማ መናፈሻ ፕሮጀክት፣ ከእንጦጦ ተራራ የሚነሱ 2 ዋና ዋና ወንዞችን አንደኛው 23.8 ኪሎሜትር ሌላው 27.5 ኪሎሜትር በከተማዋ ውስጥ በመጎዝ በንዋሪዎቹ ቀበና፣ግንፍሌ፣ቡልቡላ በሚል እየተጠሩ ወደ አቃቂ ወንዝ ይቀላቀላሉ፡፡ በከተማዋ ብዙ ገባር ወንዞች የሚገኙ ሲሆኑ ወንዞቹ የውሃ ብክለት ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ከባቢ አየር ለመንከባከብ የተወጠነ ሲሆን የከተማ ቱሪዝም ለማስፋፋት ታቅዶል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ቤተመንግስት ጋራዝ፣ፒያሳ፣ ውጭ ጉዳይ እያለ አቃቂ የሚደርሰው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሮል፡፡ ከወንዞቹ አጠገብ የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች፣ የእግረኛ መንገዶችና የቢሽክሌት መንገዶች ሲገነቡ፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገፅታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር ተገለጾል፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ቬርኔሮ ኩባንያ እንደሆነ ታውቆል፡፡ የአዲስ አበባ ወንዞች ዳር ተፋሰስ ልማት መንግሥታዊ ፕሮጀክት ወደ ግል ዘርፍ በአክሲዬን ለግል ባለሃብቶችና ህዝብ መሸጥ ይኖርበታል እንላለን፡፡ የህወሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት መር ኢኮኖሚ በአዲስ አበባ ከተማ ከታላቁ የሚንሊክ ቤተ- መንግሥት እስከ መስቀል አደባባይ ያለውን የህዝብ መናፈሻን ለአላሙዲን ሸጦ አጥሮ ለአለፉት 20 ዓመታት ያቆየ ፀረ ከተማ አስተዳደር የዘረጋ መንግሥት በአዲስ አበባ ይህን ዓይነት ፕሮጀክት ለመገንባት ሞራላዊ ብቃትም፣ ስነ-ምግባርም፣ ታማኝነትም የለውም እንላለን፡፡

{4} ‹‹አራት ክልሎች የተመደበላቸውን 5.3 ቢሊዮን ብር ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ እንዲያውሉ ተወሰነ›› መንግሥት ከውጭ የልማት አጋሮች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ በዘንድሮ(2011ዓ/ም)የበጀት አመት ካገኘው ስድስት ቢሊዮን ብር ውስጥ 5.3 ቢሊዮን ብር የሚከፋፈሉት አራት ክልሎች፣ ሙሉ በጀቱን ለተቀናጀ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንዲጠቀሙበት ወሰነ፡፡ ክልሎቹ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ናቸው፡፡ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ ከመንግሥታዊ ፕሮጀክት ወደ ግል ዘርፍ በአክሲዬን ለግል ባለሃብቶችና ህዝብ መሸጥ ይኖርበታል እንላለን፡፡

{5} የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለተፈናቃዬች ህዝብ፣ ለሶማሌ 35.1 ሚሊዮን ብር፣ ለኦሮሚያ 33.6 ሚሊዮን ብር፣ ለደቡብ ለ18.3 ሚሊዮን ብር፣ አማራ ክልል 4.7 ሚሊዮን ብር ፣ ትግራይ 3.9 ሚሊዮን ብር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 3.2 ሚሊዮን ብር፣ ጋምቤላ 454 ሽህ ብር፣ ድሬዳዋ 387 ሽህ ብር፣ ሐረሪ 62 ሽህ ብር በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን ብር ባንኩ ደልድሎ እርዳታ አበርክቶል፡፡ ድልድሉን የንግድ ባንክ ሥራ ሳይሆን የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን መሆን ይገባው ነበር፣ የኦህዴድ የፖለቲካ ውሳኔ ነው የሚሉ ያጋልጣሉ፣ ባንኩ ውስጥ ያሉ የኦህዴድ ፖለቲከኞች ንግድ ባንክ ውስጥ ከ50 ሹማምንቶች 31ዱን በኦህዴድ ተይዘዋል በሚል ቅሬታ ያሰሰማሉ፡፡ በባንክ አሰራር ውስጥ የፖለቲካው ጣልቃ ገብነት ባንኩን ብቃት ያላቸው ሰዎች እንዳይመሩት አድርጎል፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሲያደርግ አያውቅም፡፡ በዚህም የተነሳ የአማራ የእርዳታ አሰባሳቢ የንግድ ባንክን እርዳታ አልቀበልም ብሎል፡፡ በሃገራችን በዘር ላይ የተመሠረተው የባንክ ተቆማት መኖር ምክንያት የታዩ ክስተቶች በተለይ ተቀማጭ ገንዘባቸውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማውጣት የህወሓት የፖለቲካ ሰዎች ወደ ወጋገንና አንበሣ፣ የኦህዴድ የፖለቲካ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ህብረት ሥራና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናልና፣ አዋሽ ባንኮች፣ የብአዴን የፖለቲካ ሰዎች ደግሞ ወደ ዓባይና አቢሲኒያ ባንኮች በማዘዋወር የንግድ ባንክ ከፍተኛ ኪሳራ ይከናነባል የሚል ስጋት አለ፡፡ በሃገሪቱ ባንኮች አክሲዬናቸውን ለአንድ ዘር ብቻ በመሸጥ የዘር ባንኮች መስፋፋታቸው ይታወቃል፡፡ የባንክ ተቆማት ከፖለቲካ፣ ከዘር፣ ከኃይማኖት ወገንተኝነት ተላቀው እንዲሰሩ አዲስ መመሪያ መውጣት ይኖርበታል እንላለን፡፡

{6} የአገሪቱ ባንኮች ለሦስት ፕሮጀክቶች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ሊያዋጡ ነው 17 March 2019
የአገሪቱ ባንኮች ለሦስት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ከ2010 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፋቸው 2.5 በመቶ የሚሆነውን ለመስጠት ተስማሙ፡፡ በዚህም መሠረት ልማት ባንክን ሳይጨምር የአገሪቱ ባንኮች ለሦስቱ ፕሮጀክቶች 400 ሚሊዮን ብር ገደማ ያዋጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንደኛው፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ ለተፈናቃዮች ለማዋል የታሰበው የገንዘብ መጠን እያንዳንዱ ባንክ ባለፈው የሒሳብ ዓመት ካገኘው የተጣራ ትርፍ 0.5 በመቶ በማስላት ገቢ ያደርጋል፡፡ ሁለተኛው፣ የአንቦ ስታዲዮም ግንባታም እያንዳንዱ ባንክ በተመሳሳይ ከባለፈው የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ 0.5 በመቶ ወይም አንድ ሚሊዮን ብር ገቢ ያደርጋል፡፡የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚውል ሲሆን፣ ለዚህ ፕሮጀክት ባንኮቹ የተስማሙበት መጠን ከባለፈው የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፋቸው 1.5 በመቶ የሚሆነውን በማስላት፣ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ገቢ የሚያደርጉት እንደሆነ ከማኅበሩ ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ይህ ውሳኔ የአገሪቱ ባንኮች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ተፈጻሚ የሚያደርጉት ስለመሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ለሦስቱም ጉዳዮች የሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ ከ2010 የሒሳብ ዓመት የተገኘውን ትርፍ በማስላት ገቢ የሚያደርጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ 1.5 በመቶ ቢሆንም፣ ገንዘቡን ገቢ የሚያደርጉት ግን በሦስት ዓመት ማለትም 0.5 በመቶ የተጣራ ትርፋቸውን በማስላት ይሆናል፡፡ የባንኮቹ ይፋዊ የ2010 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ 16 የግል ባንኮች ከታክስ በፊት 10.48 ቢሊዮን ብር፣ ከታክስ በኋላ ደግሞ 8.1 ቢሊዮን ብር አትርፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 10.32 ቢሊዮን ብር ያተረፈ ሲሆን፣ ከታክስ በኋላ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ሳይጨምር 17 ባንኮች በጥቅል ያተረፉት ከታክስ በፊት ከ20.7 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሌሎች ተቀናሾች ሳይካተቱ ከታክስ በኋላ ያገኙት ትርፍ በጥቅል ሲታይ ወደ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ልማት ባንክን ሳይጨምር የአገሪቱ ባንኮች ለሦስቱ ፕሮጀክቶች 400 ሚሊዮን ብር ገደማ ያስገባሉ ማለት ነው፡፡ ሁሉም የአገሪቱ ባንኮች ለሦስቱም ፕሮጀክቶች የሚሰጡትን ገንዘብ ገቢ የሚያደርጉት በማኅበሩ የአዋሽ ባንክ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው፡፡ ኦህዴድ/ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርገው ብድር ሀገሪቱን ኢኮኖሚ መቀመቅ ይከተዋል እንላለን፡፡ የአገሪቱ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ ለአምቦ ስታዲዮም ግንባታና ለአዲስ አበባ ከተማ የወንዞች ዳርቻ ልማት የአገሪቱ ባንኮች ለሦስቱ ፕሮጀክቶች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲያዋጡ ማስገደድና ጣልቃ መግባት የፋይናንስ ባንክ ዘርፉን መቀመቅ ይከተዋል እንላለን፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት በባንኮች አሠራር ላይ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መቆም አለበት እንላለን፡፡

ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹማምንት ፖለቲከኞ ሹማምንቶች ቃለ-መጠይቅ ጥናታዊ ትንተናችንን እናጠናቅቃለን፣
ጥያቄ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹማምንት ፖለቲከኞች ናችሁ፡፡ ባንኩ ከፖለቲካው ምን ያህል ነፃ ነው? ቀድሞም ሆነ አሁንም የገዥው ፓርቲ አባላት የቦርድ ሰብሳቢዎች የፖለቲካ ሰዎች ናቸው፡፡ ይኼ ባንኩን በነፃነት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ እንቅፋት አይሆንም ወይ? እርስዎ በፋይናንስ ዘርፍ አቅም እንዳለዎ ጥርጣሬ ባይኖርም፣ ነገር ግን ምን ያህል ነፃ ሆነው ሥራዎን በአግባቡ ይሠራሉ?
‹‹ዶ/ር ይናገር፡- ብሔራዊ ባንክ ነፃ ነው ወይ? የሚለውን በተመለከተ እንደ አገሮች የተለያየ ተጠሪነት ነው ያለው፡፡ በተወሰኑ አገሮች ገዥው ተጠሪነቱ ለፓርላማው ነው፡፡ በአንዳንድ አገሮች ደግሞ ተጠሪነቱ ለአስፈጻሚው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም ያስኬዳል፡፡ እንደ አገሮች ነባራዊ ሁኔታ የብሔራው ባንክ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ የሚሠራበትን ሁኔታ መመቻቸት አለበት፡፡ አገራችንን በተመለከተ ከነፃነት አኳያ ዞሮ ዞሮ ይኼ ብሔራዊ ባንክ ሌላ ተልዕኮ የለውም፡፡ ዋና ዋና ተልዕኮዎቹ ሦስት ናቸው፡፡ አንደኛው የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ተመንና የውጭ ምንዛሪ ማስተዳደር፣ ሁለተኛው በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ባንኮችን መቆጣጠርና ጤናማነታቸውን መከታተል፣ ሦስተኛው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጤናማ እንዲሆን መወሰድ ያለባቸው ዕርምጃዎች እንዲወሰዱ የበኩሉን ሚና መጫወት ነው፡፡ በመሠረታዊነት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተልዕኮ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ተልዕኮዎች ስንፈጽም፣ ተልዕኮዎቹ ከመንግሥት ውጪ ሆነው የሚፈጸሙ አይደሉም፡፡ ከመንግሥት ጋር በመሆን ባሉት ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ የሚፈጸሙ እነዚህ ተልዕኮዎች ደግሞ ሌላ ዓላማ የላቸውም፡፡ ዕድገቱንና ልማቱን ለማስቀጠል ያለሙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንፃር የሚመለከታቸው የቦርድ አባላት ቢሳተፉ ባንኩ ተልዕኮውን እንዲፈጽም ያግዛሉ እንጂ፣ ብዙ ችግር ያመጣሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ ከእኛ አኳያ እስካሁን ባለው አሠራር እንደተባለው የባንክ ገዥዎችና የቦርድ አባላት በመንግሥት ተሿሚዎች መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በመንግሥት የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ ከሥራው አንፃር እኔም እዚህ በቆየሁበት ጊዜ ብሔራዊ ባንኩ ለኢኮኖሚው መፍትሔ ይሆናል ብሎ ባቀረባቸው ጉዳዮች ላይ ይኼ አይሆንም፣ ይኼ የእናንተ ጉዳይ አይደለም ተብሎ የቀረበ እስካሁን እኔ እስከማውቀው ድረስ የለም፡፡ ያቀረብናቸው ጉዳዮች በጥናት ላይ የተመረኮዙና አሳማኝ እስከሆኑ ድረስ የሚመለከታቸው አካላትም ተቀብለዋቸው እየሠራን ነው፡፡ ወደፊትም ይህንን እናደርጋለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በእያንዳንዱ ነጥብ ላይ እንደሌላው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ብሔራዊ ባንክ ውስጥ ሌላው አስፈጻሚ ብዙ የሚገባበት ሁኔታ የለም፡፡ ነገር ግን ባሉት አደረጃጀቶች በቦርድና በሌሎች ባለን ግንኙነት የባንኩን አፈጻጸም እናቀርባለን፡፡ በዚሁ መሠረት እንሄዳለን፡፡ ለፓርላማም እንዲሁ እናቀርባለን፡፡ ለቋሚ ኮሚቴ እናቀርባለን፡፡ የሚመለከታቸው ስለሆነ በዚህ ደረጃ የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴ እየመራን ነው፡፡ ስለዚህ የተነሳውን ሥጋት እኔ እንደ ሥጋት አላየውም፡፡ እንደ አገሩ ተጨባጭ ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ ››
የህወኃት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ ልማታዊ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ባንክ ኢንዱስትሪ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ቀጣይ ሆኖል፡፡ ንግድ ባንክ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ብድር እንዲያበድሩ ቀጭን ትእዛዝ ይተላለፋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ እንዳስታወቁት ‹‹በተጎተተ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ሳቢያ ከ43 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አጋጥሞል ተባለ›› ገንዘብ ሚኒስቴር በግማሽ አመቱ የታየውን የበጀት አፈጻጸም በማስመልከት ጥር 28 ቀን 2011 ዓ/ም በሰጠው መግለጫ ፣ ከ102 መሥሪያ ቤቶች የ1000 ፕሮጀክቶች ዝርዝር ሂደት የሚያሳይ መግለጫ ወይም ፕሮፋይል ተሰናድቶ ከአንድ እስከ ሰባት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የተጎተቱ ፕሮጀክቶች የ43.1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቶች መግለጫና አፈጻጸም ሂደትን የሚያመላክት ዝርዝር የክንውን ሂደትን የሚያሳይ ሰነድ እንደማይቀርብ ይናገራሉ፡፡ፕሮጀክቶቹ መቼ ጀምረው እንደሚያልቁ፣ በየዓመቱ ምን ያህል በጀት እንደተጠቀሙ፣በአካል የሚታየውና በሪፖርት የሚቀርበው አፈጻጸም አለመጣጣም፣የፕሮጀክት ክትትል ደካማነት፣ የፕሮጀክቶች ሂደት በማኅደር ተሰንዶ ክትትልና ወቅታዊ ግምገማ አለመደረግ የሰነበቱ ችግሮች ነበሩ፡፡ በዚህም ሳቢያም የጥራት፣ የመጎተት፣ያለበቂ ጥናትና አንዳንዴም ያለምንም ጥናት ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ ሥራ ሲገቡ መቆታቸው ተወስቶል፡፡ ፐረሮጀክት እንዲገነቡ ከተቆራጮች ጋር የሚገባው ውል ደካማነትም ተጠያቂነት ሲያጎድል እንደቆ ዋቢ የተደረገው ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተገቡ ውሎች ያጠቃለላሉ ተብሎል፡፡ ››

የአንድ አመት ጥናታዊ ሪፖርት (ከመጋቢት 24 ቀን 2010 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2011 ዓ/ም) ለዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት በሃገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች ታግዳሮቶችን የሚያሳይ ድጋፋዊ ሂስ፡፡

Leave a Reply