የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሀላፊነታቸውን አንዲወጡ ተጠየቀ

በትግራይ ክልል ፋብሪካዎች ያላቸው ባለሃብቶች የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በፍጥነት እንዲወጡ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ባለሃብቶቹ በትግራይ ክልል ያሉ ፋብሪካዎቻቸው አሁን ላይ በምን ደረጃ እንደሚገኙ አንደማያውቁና፤ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች ሲነገር የሚሰሙትን መረጃ ይዘው መቀመጣቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንገዶች መዘጋት፤ የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አለመጀመር፤ የባንኮች አገልግሎት መስጠት አለመጀመር፤ እና ሌሎችም አሁናዊ ሁናቴውን እንዳያውቁ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል፡፡ይህ በእንዲህ አንዳለም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአፋጣኝ ወደ ስራ ተመለሱ ብሎናል፡፡

ይህ ከመሆኑ በፊት ትክክለኛ የንብረታችንን የውድመት መጠን እና አሁናዊ ሁኔታ እንድናውቅ የትራንስፖርት፤ የባንክ፤ የስልክ እና መሰል አገልግሎቶች ይጀመርልን ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዮሐንስ ድንቅአየሁ በበኩላቸው  የተጠቀሱት አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በሙሉ አቅማቸው  ወደስራ እንዲገቡ ምክክር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋቋመው የወደሙ ንብረቶች አጣሪ ግብር ሃይልም ስለወደሙ ንብረቶች ሪፖርቶችን በማዘጋጀት የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሚያቀመጥ ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

*****************************************************************************

ዘጋቢ፡ቤዛዊት ግርማ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply