የመንግስት ተቋማትና ክልሎች ቃል የገቡትን የገንዘብ ድጋፍ ገቢ ካላደረጉ የእንቦጭ አረምን የማስወገድ ስራውን ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሀ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰው ሀይል እና በማሽን በመታገዝ  በጣና ሀይቅ  ላይ የተጋረጠውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ በተደረገው እንቅስቃሴና በተሰራው የዘመቻ ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ማስወገድ እንደተቻለም ተገልጻል፡፡የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ ለአሀዱ እንደተናገሩት የእንቦጭ አረምን የማስወገድ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ዘመቻውን በጥር ወር መጀመሪያ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቅቀ ውጥን ተይዞ እየተሰራ መሆኑንንም ተናግረዋል፡፡የእንቦጭ አረምን የማስወገድ ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡ የተለያዩ የመንግሰት ተቋማት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ክልሎች ገንዘቡን ገቢ ያለማድረጋቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡አብዛኛው ስራ ተጠናቆ የሚቀሩት ጥቂት ስራዎች መሆኑን የተናገሩት ዶክተር አያሌው የተገኘው ውጤት አበረታች በመሆኑ የተጀመረው ስራ ሳይቋረጥ መጨረስ እንዲቻል ሁሉም የበኩሉን ሀላፊነት ሊወጣ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

***************************************************************************

ቀን 12/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply