የመንግስት ተቋማት መንግስታዊ ገንዘብን ከንግድ ባንክ ውጭ ማስቀመጥ የለባቸውም መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል። ባህርዳር:- ሚያዚያ 03/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የመንግስት…

የመንግስት ተቋማት መንግስታዊ ገንዘብን ከንግድ ባንክ ውጭ ማስቀመጥ የለባቸውም መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል። ባህርዳር:- ሚያዚያ 03/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የመንግስት በጀት በብዛት በግልባንኮች ማስቀመጥ የተለመደ ሆኗል። የግል ባንኮች ለመንግስት ሰራተኞች ከተቋማት ጋር ውል እየያዙ ገንዘብ ለተሽከርካሪ፣ ለቤት እና ለዕቃ ማበደራቸው፣ አገልግሎታቸው ፈጣን በመሆኑ ብዙዎች ይመርጧቸዋል። በተለይም ከ2010 ዓም በሗላ ንግድ ባንክ የፖለቲካ ማዕከል በመሆኑ ለአንድ ወገን ያዳላል በመባሉ ብዙዎች ወደ ግል ባንክ ዙረዋል። የአማራ ክልል ንግድ ባንክ ለተፈናቃዮች እንደ ሌሎች ክልልሎች አልረዳም በሚል ወደ ግል ባንክ አዙሯል። ከዚህ ባለፈም ንግድ ባንክ በኦህዴድ ብልፅግና አማካኝነት የንግድ ባንክ አስተዳድሩ እና የገንዘብ ፍሰቱ ወደ አንድ ወገን አዘንብሏል የሚል ወቀሳ አለ። ወቀሳውን ተከትሎ ብዙ መስሪያቤቶች በጀታቸውን ወደ ግል ባንክ አዙረዋል። የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ከ90 ከመቶ በላይ በጀታቸውን በአዋሽ፣ በኦሮሚያ ኮርፖሬት እና በኦሮሚያ ባንክ በኩል ያሳልፋሉ። በአማራ ክልል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 40 ከመቶ አካባቢ ተቋማት ወደ ግል ባንኮች ዙረዋል። አሁን አሁን ደግም የሀይማኖት ባንኮች የበለጠ እየመጡ ነው። የብሄር ባንኮችም እየጨመሩ ነው። ይሄ በመሆኑም ብዙው ገንዘቡን ወደ ወገነው ማስቀመጥን መርጧል። ይህ ሂደት የሀገር ሀብት የሆነውን ንግድ ባንክን ያዳክማል ቢባልም፣ በንግድ ባንክ ውስጥ ያለው አሰራር ሚዛናዊ መሆን ይገባዋል። የፋይናንስ ሚኒስቴር ከወር በሗላ ገንዘባቸውን በመንግስት ባንኮች ያላደረጉ ተቋማት በጀት አይመደብላቸውም ብሏል። ይሄን ሁኔታ አንዳንዶች የነፃ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ይጎዳል የሚል ሀሳብ እየሰጡ ነው። የግል ባንኮችን እያቀጨጨ መንግስት ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር እያሰበ ይመስላል እየተባለ ነው። በአማራን መሰረት ያደረጉ ፀደይ፣ ፅሃይ፣ አማራ፣ ጃኖ የተባሉ ባንኮች በምስረታ ሂደት ላይ ናቸው። አማራ ባንክ በሀገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ ቢያሰባስብም ወደ ስራ ለመግባት ግን ውስጣዊ ችግር እንደገጠመው እየተነገረ ነው። ጃኖ ባንክ ደግሞ መስራቾች ቢሮ ዘግተው ጠፍተዋል የሚል ወቀሳ እየቀረበባቸው ነዉ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply