የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዢ ከ20ሺህ በላይ የንግዱ ማህበረሰብ በዘርፉ እየተወዳደሩ ነው አለ፡፡የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን የኤሌክትሮኒክስ ግዢ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/vALnIGQ2Lh_9HcPDUZrXZnVf1BQANXlUulmIFYSka8ldBBcgBskor7kNEnjgmibbH0zQ47YlUpcUGPJNIshlNLDvVNqKnn_8Rsi5pQVYctC8RfegPG-Xfsr3wjvrCzGqOBnVzOi6CuiEEG5KH4PkmjJXaf_9VwxOzA7lXBY3XF1CzBO2Jiy4qCmeO8-yMEafs60YYgUBv0gk1i6MMZoGLtwi32yeHoaNrqRvJsGexGhbg1a8UdUY_8w-FCLWQfy_2amrp-SYI_YMxQzzR2746TG6m3aVnDZ0kAhKvZ5jltNXGYEDLBqa3G9eNNCohBpFgfuItuSgaObwvoZHXFdHUg.jpg

የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዢ ከ20ሺህ በላይ የንግዱ ማህበረሰብ በዘርፉ እየተወዳደሩ ነው አለ፡፡

የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን የኤሌክትሮኒክስ ግዢ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ታደሰ ከበደ ለጣቢችን እንዳሉት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስረዓትን በመከተል ከ20ሺህ በላይ የንግድ ተጫራቾች እየተወዳደሩ ነው ተብሏል ።

በንግድ ፍቃድ ደረጃ ደግሞ ከ60ሺህ 59 በላይ የንግዱ ማህበረሰብ በስርዓቱ የተመዘገበ መሆኑንና አዳዲስ ማህበረሰቦችም ስረዓቱን እየተቀላቀሉ መሆኑን ነግረውናል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገራችን ክፍሎች በስተቀር ሁሉም የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ግዢ እንደሚገበያዩ ተገልጿል ።

እንዲህ ያለው አሰራር ብልሹ አሰራርን ከመስቀረት አንፃር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም አቶ ተደሰ ከበደ ተናግረዋል።

በልዑል ወልዴ

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply