የመኖሪያ ቤት ዕድሳት ፈቃድ ለመስጠት ጉቦ የጠየቀ የወረዳ አስተዳደር ሰራተኛ 10 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ መርዕድ ክበበ ይባላል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ ባለሙያ ነው፡፡

አቶ በድሉ አለማየሁ የተባሉት የግል ተበዳይ ቤታቸውን ለማደስ ፈልገው የእድሳት ፈቃድ ለማውጣት ወደ ወረዳው ቀርበው በጠየቁበት ወቅት ተጠርጣሪው ምክንያት እየፈጠረ በማመላለስ ማሳደሻ ፈቃዱን መውሰድ ከፈለጉ 10 ሺህ ብር እንዲሰጡት መጠየቁ ታውቋል፡፡

የግል ተበዳይም ሁኔታውን ለፖሊስ በማሳወቅ እና ፖሊስም ክትትል በማድረግ ብሄረ ፅጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መርዕድ ክበበ ከአቶ በድሉ አለማየሁ ላይ 10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሌብነትን ለመዋጋት የተጀመረው ሃገር አቀፍ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ እያሳየ ያለው ተባባሪነት የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ መረጃ እና ጥቆማ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply