የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው እንደሚገኝ ተነገረ፡፡  አሻራ ሚዲያ ህዳር፤4/03/2013/ ዓ.ም ባህር ዳር  የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን…

የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው እንደሚገኝ ተነገረ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፤4/03/2013/ ዓ.ም ባህር ዳር የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን…

የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው እንደሚገኝ ተነገረ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፤4/03/2013/ ዓ.ም ባህር ዳር የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው እንደሚገኝ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናንት ጀነራል አስራት ዴኔሮ ገለፁ፡፡ ሌተናንት ጀነራል አስራት ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከምሁራን ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ፅንፈኛው ሀይል ህወሃት በሠራዊቱ ላይ ያሴረውን ሴራ ባለፉት ሁለት ዓመታት የራሱን ሀይል እንዴት እንደገነባ ፣ የሀገር ክህደቱንና የፈፀማቸውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዲሁም ሠራዊቱ ሲያከናውን የቆየውን ህዝባዊ ተግባራት አብራርተዋል፡፡ ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት እያከናወነ ባለው ህግ የማስከበር ለሀገር ህልውና ዘመቻ በጥንቃቄ ፣ በሰለጠነና ሙያዊ በሆነ መንገድ በህዝብ እና በልማት ላይ ጉዳት ሳያስከትል እየፈፀመ ይገኛል ብለዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊቱ ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች በተለይም በማይካድራ እና በሽራሮ እንደሚሸነፍ ሲረዳ ገዳይ ቡድን በመመደብ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ እና የእርስ በርስ ግጭት ለማስነሳት እየጣረ ይገኛል ብለዋል፡፡ ህገ ወጡ የህወሃት ቡድን የሃገር መከላከያ ሠራዊቱን በየትኛውም ታክቲክ ሊዋጉት የሚያስችል ቁመና እንደሌላቸውም አስገንዝበዋል፡፡ ዘጋቢ፡ ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply