የመከላከያ ሰራዊቱ ሁሉንም ዓይነት የውጊያ ስልቶች በቅንጅት እየተጠቀመ አመርቂ ድል እያስመዘገበ ነው ተባለ፡፡             አሻራ ሚዲያ       ህዳር፡…

የመከላከያ ሰራዊቱ ሁሉንም ዓይነት የውጊያ ስልቶች በቅንጅት እየተጠቀመ አመርቂ ድል እያስመዘገበ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡…

የመከላከያ ሰራዊቱ ሁሉንም ዓይነት የውጊያ ስልቶች በቅንጅት እየተጠቀመ አመርቂ ድል እያስመዘገበ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-19/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር የመከላከያ ኃይል ሁሉንም ዓይነት የውጊያ ስልቶች በቅንጀት በመጠቀም ጠላት የተማመነባቸውን የተራራ ላይ ምሽጎች ደረማምሶ አመርቂ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑን ሜጀር ጀኔራል ዓለምሽት ደግፌ ገልፀዋል፡፡ ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያሰማራቸው ሃይሎች በተራራ ሰንሰለቶች ግርጌ ጠንካራ ምሽጎችን ገንብተው ለመዋጋት ቢሞክሩም የመከላከያ ሰራዊትን ጠንካራ ምት መቋቋም ግን አልቻሉም ነው ያሉት ጀኔራል ዓለምሸት፡፡ በዚህም በርካቶች ከነ ትጥቃቸው ሲደመሰሱ ቀሪዎቹ ደግሞ ሸሽተው እና ተማርከው ምሽጎቹን መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ ቀሪዎቹን ግዳጆች በብቃት ለመወጣት በሰው ሃይል እና በውጊያ ቅንጅት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን የጠቆሙት ጀኔራል ዓለምሸት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህዝባችን የድል ብስራት ዜና እናሰማለን ነው ያሉት፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply