የመከላከያ ሰራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አደረገ

የመከላከያ ሰራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አድርጓል።
በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡
የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ማምሻውን እንዳስታወቀው የመከላከያ ሠራዊት ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ በኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

The post የመከላከያ ሰራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply