የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።ኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ምልክቶች ሀገራዊና ታሪካዊ ይዘታቸው የ…

የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

ኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ምልክቶች ሀገራዊና ታሪካዊ ይዘታቸው የጎላ እንዳልነበርም አምኖ፣በምልክቶቹ ጋሻና አንበሳን ጥቅም ላይ ማዋሉን ነው የገለጸው።
 
ሰራዊቱ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ካስፈለገ፤ አርማውም ማዕረጉም ስርዓት ሲለወጥ መቀየር የሌለባቸው ሆነው እንዲቀመጡ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማእከል ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል መስፍን ለገሰ እንዳሉት አዲስ የተሻሻሉት ወታደራዊ የማዕረግ ምልክቶችም ሀገራዊ እና ታሪካዊ ይዘቶችን ከግምት ያስገቡ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
 
የሠራዊቱ የማዕረግ ምልክት በዋናነት አንበሳውን ሰራዊታችንን እና ህዝባችንን በሚገልፀው የአንበሳ ምልክትና የአገር ሉዓላዊነትና ክብር የማስጠበቃችን ምልክት የሆነውን ጋሻ እንዲያካትት ተደርጎ መዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡
ሠራዊት ዘመን ተሻጋሪ መሆን ካለበት ዓርማውም ፣ ማዕረጉም ፣ ሌሎችም ነገሮች ስርዓት ሲለዋወጥ መቀየር እንደማይገባም በመግለጫው ተመልክቷል።

ታህሳስ 29 ቀን 2014

ኢትዮ ኤፍ ኤም  107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply