የመከላከያ ሰራዊት ወሳኝ የተባሉ ድሎች

የመከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ የሚያፋጥኑለትን ድሎች እያገኘ መሆኑን አሳወቀ።
ሰራዊቱና የአማራ ክልል የፀጥታ አባላት ኅዳር 8 በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ የተባሉ ድሎችን መቀዳጅታቸው ተነግሯል።
የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ “በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል። ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሰራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው” ሲል አሳውቋል።
በምዕራብ ግንባር በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም በመገስገስ ላይ ስለመሆኑም ተገልጿል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ክልል የፀጥታ አባላት የሕወሓት ታጣቂ ቡድን ጥቅምት 24 ምሽት በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ እና በአማራ ክልል ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ የጀመሩት የመከላከል፣ መልሶ የማጥቃት እና ግቡን የሕወሓት የበላዮችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሕግን የማስከበር እርምጃ 2 ሳምንት ሞልቶታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply