የመከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህወሓት ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1…

የመከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህወሓት ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህውሓት ታጥቂ ቡድን አባላት መደምሰሳቸው ተገለፀ። በተጨማሪም 29 የልዩ ሃይል እና ሚኒሻ አባላትም ተማርከዋል። የፅንፋኛው ህውሓት ታጣቂ ቡድን በዚህ በግንባር ከፍተኛ ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑም ተነግሯል። እስካሁንም 115 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 11 መትረየስ፣ 2 ድሽቃ፣ 8 አር ፒጂ ከባድ መሳሪያ፣ 152 የእጅ ቦንብ፤ 2 ስናይፕር፣ 4 ኤም-14 ጦር መሳሪያ፣ 2 ኢንኮም ሬድዬ ተማርኳል። በተጨማሪም 21 ሺህ 650 የክላሽ ጥይት፣ 14 ሸህ 730 የመትረየስ ጥይት፣ 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 64 የጦር ሜዳ ቀበቶ፣ 6 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ፣ 90 የክላሽ መጋዘን እና 10 የመትረየስ ዝናር ተማርኳል። እንዲሁም ከስሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ተዘርፈው የነበሩ 5 ታንኮች ሲመለሱ አንዱ ወድሞ፤ አንድ ታንክ በጠላት እጅ ይገኛል። የስሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም፥ ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግራዋል። የሰራዊቱ ተልእኮን የመፈፀም ብቃት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ዋና አዛዡ፥ ስራዊቱ ዳንሻ ትርካን ዲቪዥን ባእኸር ራውያንን እና የሁመራ ከተሞችን መቆጣጠሩንም ተናግረዋል ሲል የዘገበው ዋልታ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply