የመከላከያ እና የልዩ ሃይል ልብስን በመልበስ በወንጀል ድርጊት ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸው ተነገረ፡፡
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የመከላከያን እና የልዩ ሃይልን የደንብ ልበስ ለብሰው ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሃብታሙ አሰፋ፣ ግለሰቦቹ ከጅማ እና ከዳውሮ ወደ ወላይታ ሶዶ የሚመጡ መኪናዎችን በማስቆም ዝርፊያ ሲፈፅሙ እንደነበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ የወንጀል ድርጊቱን ሲፈፅሙ የነበሩት መኪናዎችን አስቁመው በስለት መሣሪያ በማስፈራራት መሆኑን የፖሊሲ አዛዡ ገልጸዋል።
ሃምሌ 17 ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ወንጀሉን ሲፈፅሙ ከነበሩት መካከል መልካሙ መና እና አለማየሁ ሻንጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
የተቀረው አንድ ተጠርጣሪ ያመለጠ ሲሆን የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡን ለመያዝ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ይህ ተግባር በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን የመከላከያ ሃይልን ክብር የሚያወርድ ነው ያሉት ምክትል ኮማንደር ሃብታሙ አሰፋ፣ መሰል ድርጊቶች እንዳይደገሙ አስተማሪ እርምጃ እንደሚሻ ገልጸዋል።
የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት እንደገለፀው ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ድርጊቶች ሲፈፅሙ እንደነበር ተረጋግጧል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
ነሃሴ 02 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos