
የመከላከያ ዩኒፎርም እና ሲቪል በለበሱ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው በሌሊት ታፍነው የተወሰዱት ሙላት ከፋለ እና ብርሃኑ ንጉሴ አለሙ የተባሉ አማራዎች አድራሻቸው በትክክል ሳይታወቅ አንድ ሳምንት አልፏል፤ ቤተሰብ አሁንም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከሀምሌ 5/2015 ምሽት ጀምሮ በከፍተኛ ጭንቀት እና ፍለጋ የሰነበቱት የሙላት ከፋለ ቤተሰቦች አዲሱ ቤተ መንግስት እየተገነባ ባለበት አካባቢ በድብቅ ታግቶ እንደሚገኝ ያልተጣራ መረጃ ደርሶናል ይላሉ። ነገር ግን አሁንም እርግጠኞች አይደሉም፤ በሰላማዊ ቤተሰባቸው በግፍ ታስሮ አድራሻውን የማጥፋት ሁኔታ በእጅጉ አሳስቧቸዋል፤ አሁንም መቆሚያ፣ መቀመጫ እና እረፍት ከነሳቸው ጭንቀት አልተገላገሉም፤ በተደጋጋሚ የአፋልጉን ጥሪ እያቀረቡ ነው። ከየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ከሀምሌ 5/2015 ከምሽቱ 5:40 ሰዓት ጀምሮ ከመኖሪያ ቤቱ በአንድ የመከላከያ ሰራዊት ልብስ በለበሰ እና ስድስት ሲቪሎች ታፍኖ የተወሰደው ብርሃኑ ንጉሴም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከተፈጸመበት አፈና አልተለቀቀም፤ ያለበት አድራሻ እንኳን በትክክል የሚናገር አልተገኘም። ቤተሰቦቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ የመኖር ዋስትናችንን እና ተስፋችን እየተሟጠጠ ይገኛል ሲሉ በሀዘኔታ ተናግረዋል፤ ቢያንስ ያፈነ አካል አድራሻቸውን እንዲነግራቸው ጠይቀዋል።
Source: Link to the Post