የመጀመሪያዉ የጦር መርከብ ከቱርክ ሞቃዲሾ ደርሷል፡፡

ቱርክ እና ሶማሊያ በገቡት የ10 ዓመት የወታደራዊ ስምምነት መሰረት የመጀመሪያዉ የጦር መርከብ ትናንት ማክሰኞ ሞቃዲሾ መድረሱ ተሰምቷል፡፡

የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሀመድ ከቱርክ ለመጣዉ የጦር መርከብ በተደረገ የአቀባበል ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ ነበር፡፡

ከቱርክ ጋር ያለዉ ስትራቴጂያዊ ትብብር ላይ ትኩረት ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በደህንነት፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ከቱርክ ጋር እንዳላቸዉ ነዉ ያነሱት፡፡

ፕሬዝዳንቱ ወንድማዊ እና ታማኝ አጋር ነዉ ሲሉ ለቱርክ መንግስት ያላቸዉን ምስጋናም ገልጸዋል፡፡

ለ10 ዓመት ይቆያል የተባለዉ ይህ ስምምነት በሶማሊያ ፓርላማ ሙሉ ፍቃድ አጊኝቶ በፕሬዝዳንቱ ተፈርሞ የጸደቀ ነዉ፡፡

ስምምነቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠናክር ነዉ የተባለ ሲሆን፤የቱርክ የነዳጅ አዉጪዎች በሶማሊያ ያለዉን ነዳጅ እንዲያወጡም የሚያስችል ዕቅድ በዉስጡ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ባደረገችዉ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ዉጥረት ዉስጥ በገባችበት ሰዓት የተደረገ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply