
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጉባዔው በኢትዮጵያ ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን፤ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ካዘጋጀው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡
በጉባዔው ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ 44 ያህል ፕሮጀክቶች በመንገድ ልማት፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በባቡርና በአየር ትራንስፖርት መስኮች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሊጣመር በሚችልባቸው እድሎች ላይ ምክክር ይደረጋልም ነው የተባለው።
የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
The post የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post