You are currently viewing የመጀመሪያ ዙር የስራ ማቆም አድማ ከሕዳር 30/2015 ጀምሮ የተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በመግለጫቸው አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የመጀመሪያ ዙር የስራ ማቆም አድማ ከሕዳር 30/2015 ጀምሮ የተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በመግለጫቸው አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የመጀመሪያ ዙር የስራ ማቆም አድማ ከሕዳር 30/2015 ጀምሮ የተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በመግለጫቸው አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ:_ ለሁሉም ሚዲያዎች ባሉበት ጉዳዩ_የመጀመሪያ ዙር የስራ ማቆም አድማ ከሕዳር 30/2015 ጀምሮ የተጠናቀቀ መሆኑን ስለማሳወቅ። እንደሚታውቀው ከህዳር 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት 5 ቀናት በኢትዮጵያ በሚገኙ ሰላሳ ስምንት/38 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሰቲዎች) በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ የማቆም አድማ ተደርጓል። የስራ ማቆም አድማው አላማም የመምህራን ፍትሀዊ የኢኮኖሚ፣ የክብር እና የህልውና ጥያቄዎችን በመንግስት ተግባራዊ ምላሽ እንዲሰጠን በህገ መንግስቱ መሠረት ጥያቄ ለማቅረብ ነው፡፡ በዚህ አድማ በአብዛኛው ዩኒቨርስቲዎች ሙሉ በሙሉ የመማር ማስተማር ስራው ለአምስት 5 ተከታታይ ቀናት ተቋርጧል። በዚህ የስራ ማቆም አድማ ወቅት የችግሩ ሰለባ የሆኑት መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በሚደንቅ ተሳትፎ እና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጀመሪያው ዙር የስራ ማቆም አድማ የተጠየቁ ጥያቄዎች ባይመለሱም እጅግ በጣም አበረታች ተግባራትን ማሳካት ተችሏል። በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ከታሰሩብን መምህራን ውጭ ምንም አይነት ጉዳትም ሆነ መስተጓጎል እንዳልገጥመን ለመገምገም ተችሏል። ውድ መምህራን:_ የመጀመሪያው ምዕራፍ የስራ ማቆም አድማ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተማሪዎች ተግቢውን ምክር በመስጠት፤ ከረብሻ እና ከብጥብጥ እንዲርቁ ከአጀንዳችን ዉጭ ሌላ አላማ ያላቸዉ አካላት መጠቀሚያ እንዳይሆኑ እና መንግስት በግምገማው የፈራዉን ድርጊት መቆጣጠር መቻላችን እጅግ አርቆ አሳቢ፣ ለሀገር ተቆርቋሪ እና ኢትዮጵያ የምትኮራብን ትዉልድ አፍሪዎች መሆናችንን የሚገልጽ ነው። ውድ ተማሪዎቻችን:_ የመምህራን ችግር ገብቷችሁ በብዙ ነገር ስለተባበራችሁን በጣም እናመሰግናለን። በዚህ ትግል ትምህርት ሚኒስቴር ከ360 በላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ፍተሻ ለማድረግ መወሰኑ እና ከህዳር 30 ጀምሮም ፈቃድ መከልከሉ ለተማሪዎቻችን የተገኘ የትግሉ እመርታ መሆኑንና በቀጣይም ለተማሪዎቻችን የተሻለ ዕድል መታገላችንን እንቀጥላለን። በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተወሰኑ ተማሪዎቻችን ለተለየ የፖለቲካ ተልዕኮ በማስያዝ ወደ አላስፈላጊ ብጥብጥ እንዲገቡ በመገፋፋት የመምህራኑና የቴክኒካል ረዳቶችን ጥያቄዎች ፖለቲካዊ ይዘት ለማስያዝ የሚሰሩ እኩይ አካላት መኖራቸውን በመረዳታችን ቀጣይ የትግል መርሆችን እና አቋም መግለጫዎችን ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ ከመገኘቱም በላይ ቀጣይ ትግላችንን ከፍ አድርገን ለማቀጣጠል የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጠናል። 1.መሪ የለውም የተባለውን የስራ ማቆም አድማ ሁሉም መምህር በባለቤትነት መሪና ተመሪ በመሆን የህግ፣ የኮሚኒኬሽን፣ የአይቲ፣ የአደጋ መከላከል እና የስነ ቋንቋ ክፍሎችን በማቋቋም የመጀመሪያ ዙር ስራዎችን በሚገባ በማስኬዳችን እና ለቀጣይ ትግል ጥሩ መሰረት በመጣላችን በዚህ ታሪካዊ ስራ የተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን። 2.መንግስት ጥያቄወቻችን በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመልስልን የእፎይታ ጊዜ በመስጠት የኛን መሰረታዊ ፍላጎቶች እንዲያሟላ ምሁራዊ ምክራችንን እናቀርባለን፡፡ የግል ከፍተኛ የትምሀርት ተቋማት ላይም አስቸኳይ የማጣራት ተግባራት እንዲከናወን እንጠይቃለን፡፡ 3. በ04/04/2015 ዓ.ም ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት በሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በቦርድ አመራር ሰብሳቢነት በ03/04/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን እንዲሰበስቡ ከተቻለ ደግሞ የሃገሪቱ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) በበይነ መረብ ሁሉንም መምህር በክብር እንዳያወያዩ እንይቃለን። 4) የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ለነበራችሁ ተሳትፎ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብን ከ04/04/2015 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማሩ ሂደቱ ይቀጥላል፤ የመምህራን ማህበር የሌለባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መምህራን በአጭር ጊዜ እንዲያቋቁሙ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንድትተባበሯቸው እንጠይቃለን። 5. መንግስት ህገ መንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን ባደረግነው የስራ ማቆም አድማ ሰበብ በማንኛዉም ከፍተኛና መካከለኛ አመራር፤ መምህር እና ቴክኒካል ረዳት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ፣ ከስራ ማገድ፣ የማሰር እና ሌሎች እንግልቶች እንዳይፈጠሩ ለማሳሰብ እንወዳለን። 6. መንግስት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በእጁ ያሉ ጥያቄዎችን ካልፈታ የሁኔታዎች ግምገና ትንታኔ ከተሠራ በኋላ በተለየና ከፍ ባለ የትግል ስልት የምንመለስ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ 7. በተለያዩ መንገዶች የተጀመረው ውይይት፣ አንድነትን የማጠንከር ስራዎች እና ጥያቄዎቻችንን ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ይቀጥላል። መምህርነት የሙያዎች ሁሉ እናት ነዉ!!! ከሰላምታ ጋር የማይነበብ የሁሉም ዩኒቨርሲቲ መምህራን ፊርማ አለበት ሁሉም የዩኒቨርሲቲ መምህራን

Source: Link to the Post

Leave a Reply