የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ተቀዳሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ተቀዳሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆኑ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ- ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ “ሥነ ምግባርን በመገንባት እና ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚዲያ ተቋሟት ሚና” በሚል በአዳማ የአንድ ቀን መድረክ አዘጋጅቷል።

የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ በመድረኩ መክፈቻ ላይ የመገናኛ ብዙሃን የፀረ ሙስና ትግሉ በህዝብ ዘንድ የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ።

በተለይም የማህበራዊ ሚዲያ አቅም እያደገ በመጣበት በዚህ ወቅት የህዝብን ሥነ ባህሪ በሥነ ምግባር ግንባታ በማቅናት በፀረ ሙስና ትግሉ ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣም ጠይቀዋል።

የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጥቅም ላይ በማዋል እና ሌሎች የሚዲያ ተግባራት ለሃገራዊ የፀረ ሙስና ትግሉ መገናኛ ብዙሃኑ ሞራላዊ እና ሕጋዊ ግዴታቸው አድርገው እንዲወስዱትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግል ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር እና በመገናኛ ብዙሃን ሚና ዙሪያ ያተኮሩ ጥናቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ተቀዳሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply