
በግል የህክምና ተቋማት ደረጃ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የመገጣጠሚያ ህመም ህክምና በሩሁም የሩማንቶሎጅ እና የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ክሊኒክ መሰጠት ተጀምሯል ።
በአለማችን 1.6 ቢሊየን የሚሆኑ ሰዎች የመገጣጠሚያ ህመም በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ የክሊኒኩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶከተር ብርሃኑ ደመላሽ ተናግረዋል ።
በተጨማሪም በሽታው ወደ ሃገራችን ሲመጣ ከ20 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ እንደሚጠቁ ዳይርክተሩ ገልጸዋል ።
ይህንን በሽታ ለመቀነስ እና ለመከላከል እንዲያስችል “ሩሁም የሩማንቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ህክምና ክሊኒክ ” ህክምናውን ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገራችን ጀምሯል ብለዋል።
በሃገራችን በበሽታው ላይ ከፍተኛ የሆነ የግንዛቤ እጥረት አለ ሲሉ የክሊኒኩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃኑ ደመላሽ አንስተዋል ።
ከዚህም የተነሳ በቀላሉ መቀረፍ የሚችሉ የመገጣጠሚያ በሽታዎች ፣ወደ ልብ፣ ጭንቅላት ፣ወደ ኩላሊት፣ ወደ ነርቭ እና ወደተለያዩ በሽታዎች ይሸጋገራሉ ብለዋል።
ስለሆነም የህክምናውን ተደራሽነት በማስፋት በሰዓታት ውስጥ ሊስፋፋ የሚችለውን “የሪህ ወይም የመገጣጠሚያ ” በሽታን ለመከላከል ማእከሉ ወደ ስራ መግባቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።
“ሩሁም ክሊኒክ” ይህን ህክምና አገልግሎት በአግባቡ መስጠት እንዲያስችለው በቂርቆስ ታቦት ማደሪያ አካባቢ የቂርቆስ ቴሌ አጠገብ የህክምና ማእከል መክፈቱን አስታውቋል ።
በመሳይ ገ/ መድህን
Source: Link to the Post