
የመጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ውሎ በባህር ዳር፦ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ጥቂቶች ቆራጦች ተስፋ የማይቆርጡ ወጣቶች እሁድ ዕለት በባህር ዳር ፓፒረስ አደባባይ በተደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ከመንግስት ታዛዥ የተወሰኑ ሀይሎች ጋር ተፋጠንም ታቃውማች አሰምተናል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህርዳር አስታወቀ‼️ የአማራ ልዩ ሀይል መፍረስ የለበት ብለን በመቃወማችን ።አባቶቻችን ወዳቀኗት አዲስ አበባ ለመግባት የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም ፤አማራን አጥፍታ የምትገነባ ኢትዮጵያ የለችም ፣አናውቃትም ባልን ።መንግስት ሆን አንተ የምትላትን ኢትዮጵያ አናውቃትም ብለን ጉሮሮአችን እስኪደርቅ በጮህን ።ወልቃይት ፣ራያ ፣ደራ እና መተከል የማንደራደርባቸው የአማራ አፅመ ርስቶቻችን ናቸው ብለን ስንጮህ ፤የራሳችን ወንድሞች በሆኑት የአድማ ብተና ሀይል በባህር ዳር ከተማ ፓፒረስ አደባባይ የፈፀሙት እጅግ አሳፋሪ ተግባር እናወግዛለን ። የእኛ ጩኸትና ተቃውሞ የእናንተም መሆን ነበረበት ።በቀጣይ ለሚደረጉ ህዝባዊ ንቅናቄዎች የህዝባዊ ንቅናቄው አካል እንደምትሆኑ ፣ትላንት የሰራችሁትን አስነዋሪ ተግባር በቀጣይ እንደማትደግሙት እንዲሁም ወደ ቀልባችሁ እንደምትመለሱ ፤ከህዝባችሁ ጎን እንደምትቆሙ ተስፋ በማድረግ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር በቀጣይ ጊዚያት ለሚደረጉ የአማራ ህዝብ ሁሉን አቀፍ የህልውና ትግል አጋር ትሆኑ ዘንድ የከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል ። በዚህ አጋጣሚ መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ፣የሰላማዊ ሰልፍ ከህዝባችሁ ጎን ለነበራችሁ ጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል እና የህዝባዊ ፖሊስ ሰራዊት አባላት የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ላደረጋችሁት ህዝበኝነት ፤ ታላቅ የአጋርነት ተግባር ያለንን ልባዊ አክብሮት እንገልፃለታ። ወንድማማችነት ይጠንቅር ።ስሜታችን ስሜታችሁ ሆኖ በመገኘቱ የተሰማንን ወንድማዊ ምስጋና መግለፅ እንፈልጋለን ። ትግላችን ተጀመረ እንጂ አላለቀም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ።አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል ። ህልውናችን በክንዳችን‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post