የሚሰጡ የፍርድ ውሳኔዎች አስተማሪ አለመሆናቸው በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸም ስርቆት እንዲባባስ እያደረገ ነው….የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል
በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሃይል የሚያገኘው የህብረተሰብ ክፍል 35 በመቶ ብቻ ነው ተባለ፡፡
ለተቀረው የማህበረሰብ ክፍል የኤልክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ የማስፋፍያ ስራዎች ያስፈልጋሉ ተብሏል፡፡
የኤልክትሪክ ሃይል ለማስፋፋት ደግሞ የስርቆት ወንጀሎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን ነው የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሃይል የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን የተናገሩት፡፡
ከፍተኛ ሃይል ተሸካሚ በሆኑ የኤልክትሪክ መስመሮች ላይ የሚፈጸመው ስርቆት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የተናገሩት አቶ ሞገስ፣ ባለፈው አመት ብቻ ለስርቆት የተጋለጡ መስመሮችን ለመጠገን 100 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
አንድ የኤልክትሪክ ተሸካሚ መስመር ለመጠገን 20ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት።
እንደ ዳሬክተሩ ገለጻ ከዚህ በፊት የሃይል መስመር ስርቆት እምብዛም የማይስተዋልባቸው አካባቢዎች ሳይቀሩ አሁን ላይ ወንጀሎቹ እየተስተዋለባቸው ይገኛል፡፡
ስርቆቱን በሚፈጽ አካላት ላይ የሚሰጡ የፍርድ ውሳኔዎች አስተማሪ አለመሆናቸው ድርጊቱ እየተደጋገመ እንዲፈጸም፣ ሃገር እና ህዝብንም ለኪሳራ እየዳረገ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን