የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአራት ሚኒስትሮች ሽኝት አደረገ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዳግማዊት ሞገስ፤ ታከለ ኡማ፤ ኡመር ሁሴን እና ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኝቷል።
በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት