የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ ፡፡በጀቱ በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማስፈጸም ያለመ ነው፡፡ በተጨማሪም የሀገር…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/I0C72161pPeZM6ruL60RRLC1KmTrSO2atNB-mqwMV-vghOtpdooVuxGP-fS8cNVnn_e9igq_H_VUMKqJ4VQWb-315jxfqrGdaVcC273_xwIMb9I_adHo_cdcAVss9pE5rPUh505HHM05S-gO9boh4m2FysZnk1-9uoHIcCtqb13CamTuIX1QQk9QtVqIiT2uH6xKmzPAi_jri6Ss39dURCNcxzkjRgTDMVpnVMwREdrVeprcYHXdn_V_Hb-2dITDknJGv3eSmHe_7bApKVtYQfuBAG6a0XWk7Q_ESMgNjr6NMjq7EwnPkog_jp3Hx8mLoFBQ3EEUVCglFvp59Vb69Q.jpg

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ ፡፡

በጀቱ በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማስፈጸም ያለመ ነው፡፡
በተጨማሪም የሀገር ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመርዳትና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን መልሶ ማቋቋምን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
ምክር ቤቱም የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀትን ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ፡፡

የ2014 ዓ.ም በጀት 561 ቢሊየን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡
መረጃዉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነዉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply