የሚዲያ ለሰብዓዊ መብት ማህበር  ተመሠረተ። ማህበሩ  በሃገሪቱ ከተለያዩ  የመንግስት ና የግል መገናኛ  ብዙሃን የተውጣጡ ጋዜጠኞችን፣ካሜራ ባለሙያዎች ንና የማሥታወቂያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነ…

የሚዲያ ለሰብዓዊ መብት ማህበር  ተመሠረተ።

ማህበሩ  በሃገሪቱ ከተለያዩ  የመንግስት ና የግል መገናኛ  ብዙሃን የተውጣጡ ጋዜጠኞችን፣ካሜራ ባለሙያዎች ንና የማሥታወቂያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት  ጋዜጠኛ  በሃይሉ ጌታቸው እንደገለፀው የማህበሩ ዓላማ የ ከጊዜ  ወደ ጊዜ  እየተባባሰ የመጣውን  የሠላም  መደፍረስ ተከትሎ እየተከሠቱ ያሉ የሠብአዊ  መብቶች  ጥሰቶችን በመከላከል  ሂደት ሙያዊ ድርሻን  ለመወጣት  ነው።

ማህበሩ ሃገርና አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና ድንጋጌዎች እንዲከበሩ ና ሚዲያዎችም በትኩረት እንዲሰሩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ይሰራል ብሏል  ጋዜጠኛ  በሃይሉ።

ዛሬ በሂልተን ሆቴል በማህበሩ  የምስረታ መርሃግብር  ላይ ሰብዓዊ መብትና የሚዲያ ሚና የሚል መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ  ውይይት ተካሂዷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply