“የሚገድሉን ሰዎች እነሱ ጠንካራ ስለሆኑ ሳይሆን፣ እኛ ሞራል የለሽ እና ግድ የለሾች ስለሆንን ነው” ~~~~~~ መስከረም አበራ ~~~~~~~ በአሁኑ ጊዜ አማራ ሞቱ እንኳን አያምርም። የውሻ…

“የሚገድሉን ሰዎች እነሱ ጠንካራ ስለሆኑ ሳይሆን፣ እኛ ሞራል የለሽ እና ግድ የለሾች ስለሆንን ነው” ~~~~~~ መስከረም አበራ ~~~~~~~ በአሁኑ ጊዜ አማራ ሞቱ እንኳን አያምርም። የውሻ ሞት ነው የሚሞቱት። ቀብራቸውም አያምርም። ሞታችን አስቀያሚ፣ ቀብራችን ቀፋፊ ሆኖ እሰከ መቼ? አማራ ነኝና በዚህ እንቅልፍ የለኝም። እንደ ሰው ክብር ያስፈልገናል። የወገኔን ሞት ባልሞትም ውርደቱን ግን እጋራዋለሁ። ለምን አማራ ነኝ እኔም። እነሱ የሞቱን ፅዋ ጠጥተዋል። እኛ ውርደቱን መጋራት አለብን። እንደ ህዝብ ተዋርደን መኖር ከመረጥን ምንም ማድረግ አይቻልም። አንድ መታወቅ ያለበት ግን የምንሞተው ፈቅደን ነው። የምንሞተው በራሳችን ስንፍና ነው። የምንሞተው በራሳችን ፀብ ገላጋይ ስለሆንን ነው። የምንሞተው መብታችንን ለማስከበር የማንናበብ ስለሆንን ነው። በዚህ ሌላውን መውቀስ የለብንም። መከበር አለብን። የሰውነት ክብር ያስፈልገናል ማለት አልቻልንም። የሚገድሉን ሰዎች እነሱ ጠንካራ ስለሆኑ አይደለም። እኛ ሞራል የለሽ ስለሆንን ነው። ግድ የለሽች ስለሆንን ነው። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply